አዲስ አበባ፤ ግንቦት 12/2017(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ አዳዲስ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ወደ ስራ መግባታቸው በኮንስትራክሽን ዘርፍ ለተሰማሩ አልሚዎች ምቹ አጋጣሚ እየፈጠረ መሆኑን ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ገለጹ።
ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በድሬዳዋ ከተማ የተገነባውን የፓዮኔር ሲሚንቶ ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ማስፋፊያ ፕሮጀክት መርቀዋል።
በዚሁ ወቅት ፕሬዝዳንቱ እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ እና በቻይና ባለሃብቶች አጋርነት የተገነባው ፓዮኔር ሲሚንቶ ፋብሪካ ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ዕድገት ዘርፈ ብዙ ፋይዳ አለው።
የኢትዮጵያ እና የዓለም አቀፍ አልሚ ባለሃብቶች አጋርነት የዕውቀት ሽግግርና የካፒታል ፍሰትን እንዲሁም ምርታማነትን ማረጋገጥ የሚያስችል ሁኔታ መኖሩን የሚያመላክት መሆኑን ገልጸዋል።
ከዚህ ቀደም የኮንስትራክሽን ዘርፉ የሚያስፈልገውን ግብዓት ለማግኘት ጥልፍልፍ መንገዶችን ይጠይቅ እንደነበርም አስታውሰዋል፡፡
በኢትዮጵያ አዳዲስ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ወደ ስራ መግባታቸው በኮንስትራክሽን ዘርፍ ለተሰማሩ አልሚዎች ምቹ አጋጣሚ እየፈጠረ እንደሚገኝም አስረድተዋል።
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ኢንቨስትመንትን ማስፋፋት ሀገር የጀመረችውን የልማት ጉዞ ከማሳለጥ በላይ አዋጭ መሆኑን ጠቁመዋል።
የፓዮኔር ሲሚንቶ ፋብሪካም በስራ ዕድል ፈጠራ፣ በዕውቀት ልማትና ሽግግር ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑ ያስመሰግነዋል ነው ያሉት።
በምርቃት መርሃ ግብሩ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴን ጨምሮ የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025