አዲስ አበባ፤ ግንቦት 13/2017(ኢዜአ)፦ የኤሌክትሮኒክስ(ኢ-ሰርቪስ) አገልግሎት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመቅረፍ ለዜጎች ቀልጣፋ አገልግሎት ማቅረብ ማስቻሉን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያለማው የኤሌክትሮኒክስ አገልግሎት(ኢ-ሰርቪስ) ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተኳሂዷል።
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የኤሌክትሮኒክ መንግስት ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ሚራጅ ዘኪይ በዚሁ ወቅት በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ከተቀመጡ ጉዳዮች ውስጥ የመንግስትና ዜጎች ግንኙነትን ዲጂታላይዝድ ማድረግ አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።
የመንግስትን አገልግሎቶች በኤሌክትሮኒክስ በመደገፍ ለዜጎች ቀልጣፋ፣ ተደራሽና ግልጽ ለማድረግ የቴክኖሎጂ አሰራሮችን በማልማት ተግባራዊ ማድረግ እንደተቻለ ገልጸዋል።
እንደ ሀገር ከአንድ ሺህ በላይ የመንግስት አገልግሎቶች በኤሌክትሮኒክስ እየተሰጡ ይገኛሉ ነው ያሉት።
ቀደም ሲል የመንግስት አገልግሎት ዘመናዊ ባለመሆኑ ዜጎች ከሚያነሱት ቅሬታ ውስጥ የመልካም አስተዳደር ችግር ዋነኛው እንደሆነ አንስተዋል።
በኢንተርኔት በመታገዝ አገልግሎትን በኤሌክትሮኒክስ የሚደግፉ አሰራሮች በመተግበራቸው ለዜጎች ቀልጣፋ አገልግሎት ማቅረብ እንደተቻለና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን እየቀረፈ መሆኑን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ያስጀመረው የኤሌክትሮኒክስ አገልግሎት እንደ ሀገር ዘመናዊ አሰራርን ለመዘርጋት ከተያዘው ግብ ውስጥ አንዱ በመሆኑ የዜጎችን እንግልት እንደሚቀንስ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር እንዳሉ ሞሲሳ በበኩላቸው፤ ተቋሙ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች ውስጥ የንግድ ምልክትና የቅጅና ተዛማች መብቶች ይፋ በተደረገው የኤሌክትሮኒክስ አገልግሎት እንደሚሰጡ ተናግረዋል።
ተቋሙ ቀደም ሲል ሲሰጥ የነበረውን አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ የታገዘ ባለመሆኑ የተቋሙን አገልግሎት የሚፈልጉ ዜጎች ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በአካል መቅረብ እንደሚጠበቅባቸው አስታውሰዋል።
ይፋ የተደረገው የኤሌክትሮኒክስ አገልግሎት ተደራሽነትን በማስፋት ዜጎች ባሉበት ሆነው አገልግሎቱን ማግኘት የሚያስችላቸው ነው ብለዋል።
በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ከንግድ ምልክትና የቅጅና ተዛማች መብቶች ጋር አገልግሎት ማግኘት የሚፈልጉ ዜጎች የኤሌክትሮኒክስ አገልግሎትን በመጠቀም ያለምንም እንግልት ካሉበት ጥያቄያቸውን ማቅረብ እንደሚችሉም አስገንዝበዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025