የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የወጪና ገቢ ንግድ እንቅስቃሴን ውጤታማ ለማድረግ የባለድርሻ አካላት ሚና የላቀ ነው - ሚኒስቴሩ

May 27, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 18/2017(ኢዜአ)፦ የሎጂስቲክስ ዘርፉን ቀልጣፋና ተደራሽ በማድረግ የወጪና ገቢ ንግድ እንቅስቃሴን ውጤታማ ለማድረግ የባለድርሻ አካላት ሚና የላቀ መሆኑ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ገለጸ።

ሚኒስቴሩ ከከባድ መኪና አሽከርካሪዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር የጭነት ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ አገልግሎትን የበለጠ ማቀላጠፍ በሚያስችል ጉዳይ ላይ በሞጆ ደረቅ ወደብ እየመከረ ይገኛል።

መድረኩ የሎጂስቲክስ ስርዓቱን ቀልጣፋ እና ተደራሽ በማድረግ የገቢና ወጪ ንግድ እንቅስቃሴን ለማሳለጥ የባለድርሻ አካላትን ሚና ለማጎልበት የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።


በመድረኩ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ዴንጌ ቦሩን ጨምሮ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የሎጂስቲክስ ዘርፉን ቀልጣፋና ተደራሽ በማድረግ የወጪና ገቢ ንግድ እንቅስቃሴን ውጤታማ ለማድረግ የባለድርሻ አካላት ሚና የላቀ ነው።

ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ምርትንና አገልግሎትን ከቦታ ወደ ቦታ በማጓጓዝ በወቅቱ ለገበያ እንዲቀርብ በማድረግ በኩል ያላቸው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.