አዲስ አበባ፤ ግንቦት 18/2017(ኢዜአ)፦ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ዘላቂና አካታች የፋይናንስና የኢንሹራንስ ስርዓትን ለመገንባት ትልቅ ሚና እየተጫወተ መሆኑን የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ገለፁ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት 51ኛው የአፍሪካ ኢንሹራንስ ድርጅት ዓመታዊ ኮንፍረንስ እና ጠቅላላ ጉባኤ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ነው።
የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያን ጨምሮ በብዙ የአፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ሪፎርም እየተከናወነ ነው።
ብድርን በተመለከተ ያሉ ችግሮች ሲፈቱ የኢንሹራንስ ዘርፉን በሚፈለገው አቅም ማሳደግ እንደሚቻልም ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ እየተከናወነ ያለው የኢኮኖሚ ሪፎርም የግሉን ዘርፍ በሚያበረታታና ኢንቨስትመንትን በሚያረጋግጥ መልኩ በልዩ አመራር እየተተገበረ መሆኑን አንስተዋል።
የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራ በፋይናንስ ዘርፉ ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገትን የሚያረጋግጥ ተስፋ ሰጪ ውጤት እያሳየ ነውም ብለዋል።
በፋይናንስ ዘርፉ ህግ ከማሻሻል ጀምሮ በኢኮኖሚው ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ የሚያመጡ የአሰራር ሪፎርሞች መከናወናቸውን ጨምረው ተናግረዋል።
ባለፉት የለውጥ ዓመታት በፋይናንስ ዘርፉ የተሰሩ አጠቃላይ ስራዎች የኢንሹራንስ ዘርፉን ዕድገት በማገዝ በኩል ሰፊ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ እየተከናወነ ያለው የዲጂታል ሽግግር በአጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ ለውጥን ለማምጣትና የኢንሹራንስ ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ ከፍተኛ አበርክቶ እንዳለውም ጠቁመዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025