ደሴ፤ ግንቦት 18/2017(ኢዜአ)፦ በኮምቦልቻ ከተማ በጥራትና በፍጥነት እየተገነባ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ለከተማዋ ተጨማሪ ውበትና ለነዋሪዎች ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን የከተማዋ ነዋሪዎች ገለፁ፡፡
ከከተማዋ ነዋሪዎች መካከል ሼህ ሰይድ መሐመድ ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት በከተማው የተጀመረው የኮሪደር ልማት ግንባታው በጥራት እየተፋጠነ ከመሆኑ ባለፈ የከተማውን ውበት በማሳመር ለነዋሪዎችም ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል፡፡
ልማቱ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ በገንዘባችንና በጉልበታችን ተሳትፎ እያደረግን ነው ያሉት ሼህ ሰይድ፤ ለእግረኛ መንገድ የሚሆን ቦታ ከይዞታቸው በመልቀቅ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡
ሌላው የከተማው ነዋሪ አቶ ሳህሉ ጌቱ በበኩላቸው የኮሪደር ልማቱ ከተማዋን ገጽታ በመቀየር ለኢንቨስትመንትና ለቱሪዝም ኮንፍረንስ ምቹ ሁኔታ መፍጠር በመቻሉ መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡
በተለይ የእግረኛና የብስክሌት መንገድን ጨምሮ የአረንጓዴ ስፍራዎችንና ሌሎችንም መዝናኛዎች ያካተተ ስለሆነ ልዩ ድባብ ፈጥሯል ብለዋል።
ይህም ቀደም ሲል በትራፊክ መጨናነቅ ይደርስ የነበረውን አደጋ ከመቀነስ ባሻገር የተሳለጠ የትራንስፖርት አገልግሎት አንዲኖር የሚያስችል በመሆኑ ለግንባታው የድርሻችንን እየተወጣን ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የከተማው የኮሪደር ልማት የወደፊቱን ትውልድ ታሳቢ ያደረገ በመሆኑ ለወጣቱ ተስፋ ሰጥቷል ያለው ደግሞ ወጣት ታምራት ተመስገን ነው፡፡
በግንባታ ሂደቱም ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድል በመፍጠር በኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ተጠቃሚ እንዲሆን ያስቻለ ነው ብሏል።
የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ሚኪያስ አሊ በበኩላቸው፣ በከተማው 2ኛው ምዕራፍ የአምስት ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት በጥራትና በፍጥነት እየተሰራ ይገኛል።
እስከ ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ለማጠናቀቅ በምሽት ጭምር እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው፤ እስካሁን ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነው ግንባታ መጠናቀቁን አረጋግጠዋል።
የኮሪደር ልማቱ የብስክሌትና የእግረኛ መንገድ፣ አረንጓዴና መዝናኛ ስፍራ፣ የህዝብ መጸዳጃ፣ የህጻናት መጫወቻዎችንና የመኪና ቻርጅ ማድረጊያዎችን ጨምሮ ሌሎችን ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል፡፡
ህብረተሰቡ በገንዘቡ፣ በጉልበቱና በሀሳቡ ከፍተኛ ተሳትፎ በማድረግ ግንባታው በጥራትና በፍጥነት እንዲከናወን ማስቻሉንም አስገንዝበዋል።
በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር በመጀመሪያው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት 2 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር መገንባቱ የሚታወስ ነው፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025