የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በብሔረሰብ አስተዳደሩ የልማት ፕሮጀክቶች ጊዜና ጥራታቸውን ጠብቆ በማጠናቀቅ የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ እየተሰራ ነው

May 28, 2025

IDOPRESS

ሰቆጣ ፤ግንቦት 19/2017 (ኢዜአ)፡-በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የልማት ፕሮጀክቶች ጥራታቸውን ጠብቆ በጊዜ በማጠናቀቅ የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን የአስተዳደሩ ተቀዳሚ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሃይሉ ግርማይ ገለፁ።

የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ምክር ቤት ሲያካሂድ የቆየው 4ኛ ዙር 11ኛ ዓመት 30ኛ መደበኛ ጉባዔ ዛሬ ማምሻውን ተጠናቋል።

የብሔረሰብ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሃይሉ ግርማይ በጉባኤው ላይ ባቀረቡት ሪፖርት እንደገለጹት፣በብሔረሰብ አስተዳደሩ በግንባታ ሂደት ላይ የሚገኙ ከ100 በላይ የልማት ፕሮጀክቶች ይገኛሉ።


ከልማት ፕሮጀክቶቹ መካከል አዳሪ ትምህርት ቤት፣ የዶሮ ጫጩት ማስፈልፈያ ማዕከል፣ የጤናና የመስኖ ተቋማት፣ መንገድና ድልድዮች እንደሚካተቱበትም ተናግረዋል።

ፕሮጀክቶቹን በተያዘላቸው ጊዜና ጥራት በማጠናቀቅ የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመልስ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን እንስተዋል።

የነዳጅ እቅርቦትና ስርጭትን ጨምሮ በሌሎች ግብይቶች ላይ የሚስተዋሉ ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴን የመቆጣጠር ተግባር መከናወኑንም ነው የገለጹት።

በክልላዊና ሀገር አቀፍ ፈተናዎች ላይ ተማሪዎች የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ትምህርት ቤቶች ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ እየተደረገ ያለው ጥረትም መልካም መሆኑን አስረድተዋል።

የአካባቢውን ሰላም በዘላቂነት አጠናክሮ ለማስቀጠል ከህብረተሰቡ ጋር በተሰራው ሥራም ታጣቂዎች የሰላሙን ጥሪ በመቀበል የተሀድሶ ስልጠና በመውሰድ ወደ ህብረተሰቡ እየተቀላቀሉ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የብሔረሰብ አስተዳደሩ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋንታይቱ ካሴ በበኩላቸው በ2017/18 ለመኽር እርሻ መዳበሪያና ምርጥ ዘር አቅርቦት በወቅቱ የማድረስ ተግባር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

በነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት ላይ ህጋዊነትን የተከተለ አሰራር ሊጠናከር እንደሚገባ ጠቁመው፣ ለነዳጅ ማደያ ግንባታ ፈቃድ ያወጡ ባለሃብቶችም ፈጥነው ወደ ሥራ ሊገቡ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የአካባቢን ሰላም በዘላቂነት ማስቀጠል በየደረጃው ያሉ ምክር ቤቶች ዋነኛ ተግባር በመሆኑ የምክር ቤት አባላትና ቋሚ ኮሚቴዎች በርብርብ ሊሰሩ እንደሚገባ አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.