አዲስ አበባ፤ግንቦት 20/2017(ኢዜአ)፦ኤሌክትሮኒክስ የህዝብ ምክረ ሀሳብ መስጫና መቀበያ ስርዓት በረቂቅ ህጎች የዝግጅት ሂደት የዜጎችን ተሳትፎ በማሳደግ ግልፅና ጠንካራ ህጎችን ለማውጣት እንደሚያስችል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ተናገሩ።
ህብረተሰቡ እና ባለድርሻ አካላት በረቂቅ ህግ ላይ ሃሳብ እና አስተያየት የሚሰጡበት ኤሌክትሮኒክስ ወይም የበይነ መረብ የህዝብ ምክረ ሀሳብ መስጫ ስርዓት ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
በመርኃ ግብሩ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የፍትህ ሚኒስትር ሀና አርዓያስላሴ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ እንደገለጹት፥ መንግስት የፍትህ ዘርፉ ውጤታማ እንዲሆን በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል።
በፍትህ ስርዓቱ የህዝብና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ እንዲያድግ እና እንዲጠናከር በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝም አንስተዋል።
ዛሬ ይፋ የሆነው ኤሌክትሮኒክስ የምክረ ሀሳብ መስጫ ስርዓት በህግ ዝግጅት ላይ የህዝብ ተሳትፎ እንዲያድግ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል።
የአሰራር ስርዓቱ ዜጎች በአካል መገኘት ሳይጠበቅባቸው ባሉበት ሆነው በረቂቅ ህጎች ላይ ሃሳባቸውን እንዲሰጡ እድል የሚፈጥር መሆኑን ጠቅሰዋል።
የተዘረጋው አሰራር ከህግ አኳያ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ከማቀላጠፍ በተጨማሪ በቴክኖሎጂ ልማት እየተከናወኑ የሚገኙ ውጤታማ ተግባራትን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል።
የመንግስት ተቋማት ህጎችን በሚያዘጋጁበት ወቅት የአሰራር ስርዓቱን መሰረት በማድረግ ዜጎች በአግባቡ እንዲሳተፉ መስራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
የፍትህ ሚኒስትር ሀና አርዓያስላሴ በበኩላቸው፥ ለህግ የበላይነት መስፈን የህግ ጥራትን፣ተገማችነትን፣ወጥነትንና ተደራሽነትን ማሳደግ ቀዳሚ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ለዚህ ደግሞ በህግ ማርቀቅ ሂደት ላይ ዜጎችን በማሳተፍ ሰፊ ምክክር ማድረግ አስፈላጊ ነው ብለዋል።
ከዚህ አንጻር የተዘረጋው ኤሌክትሮኒክስ የምክረ ሀሳብ መስጫ ስርዓት ሰፊ ተደራሽነት ለመፍጠር፣ተሳትፎን ለማበረታታትና ግልጽነትን ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑን አንስተዋል።
ስርዓቱ በክልል ደረጃ አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጎ የለማ መሆኑን የተናገሩት ሚኒስትሯ፥ በህግ አወጣጥ የተሻለ ቅንጅት ለመፍጠርና ወጥነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።
#Ethiopian_News_Agency
#ኢዜአ
#Ethiopia
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025