ሀዋሳ፤ግንቦት 20/2017( ኢዜአ)፦በሀዋሳ ከተማ እየተገነባ ያለው ሁለተኛው ምእራፍ የ5 ነጥብ 6 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ስራ በመገባደድ ላይ መሆኑን የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ አስታወቁ።
ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ፤ የሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ስራ ያለበትን ደረጃ እና አጠቃላይ ክንውኑን ተመልክተዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ እንደገለጹት፥የልማት ስራዎችን መጀመር ብቻ ሳይሆን በጥራትና በፍጥነት የማጠናቀቅ ልምድ እየዳበረ መጥቷል።
አሁን ላይ የአስፋልት ንጣፍ በመከናወን ላይ እንደሚገኝ ጠቁመው፥ ግንባታው በተያዘለት ጊዜ በጥራትና በፍጥነት በመገባደድ ላይ ይገኛል ብለዋል።
የግንባታው ስኬት የክልሉ መንግስት በየደረጃው ያሉ አመራሮችና የከተማው ህዝብ የትብብርና እገዛ ድምር ውጤት መሆኑን ተናግረዋል።
ሀዋሳ በተለገሳት ተፈጥሮና በነዋሪዎቿ ብርቱ ጥረት እድገቷና ውበቷ ይበልጥ እየፈካ መሆኑን ተናግረው፥ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማትም ወደ ላቀ ምዕራፍ የሚያሸጋግራት ይሆናል ብለዋል።
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ መኩሪያ መርሻዬ፥የመጀመሪያው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ሥራ በጥራትና በተያዘለት ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት መብቃቱን አንስተዋል።
የሁለተኛው ምዕራፍ ግንባታ ደግሞ በጥራትና በፍጥነት በተሻለ መልኩ በመከናወን ላይ መሆኑን ጠቁመው፥በአጭር ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ብለዋል።
የፕሮጀክቱን አፈፃፀም በጥራትና በተሻለ ፍጥነት ለማጠናቀቅ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የድጋፍና የክትትል ሥራውን አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል።
የግንባታ ስራውን እያከናወነ ያለው ይርጋዓለም ኮንስትራክሽን ባለቤት ኢንጂነር ዘላለም ወልደአማኑኤል፥የፕሮጀክት ሥራው በጥራትና በፍጥነት ሌት ከቀን እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
የግንባታ ስራው የኮንክሪት አስፋልት፣ የፍሳሽ፣ የእግረኛና ብስክሌት መንገድ፣ የአረንጓዴ ልማትና ሌሎችም ከተማዋን የሚያዘምኑ እና የሚያስውቡ ስራዎችን ያካተተ መሆኑን ጠቁመው፥በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ መሆኑን አረጋግጠዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025