አዶላ፤ግንቦት 21/2017(ኢዜአ)፦በጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ በተለያዩ ሰብሎች ከተሸፈነው መሬት 5 ነጥብ 8 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ይጠበቃል የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ፡፡
በዞኑ በልግ አብቃይ በሆኑ 6 ወረዳዎች ከ250 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች በዘር ተሸፍኖ እየለማ እንደሆነ ተመላክቷል፡፡
በጉጂ ዞን በየአመቱ ከመጋቢት 15 እስከ ሚያዝያ መጨረሻ የዝናብና የበልግ አዝመራ የዘር ወቅት እንደሆነም ተገልጿል፡፡
የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ምክትል ሀላፊ አቶ ቂልጣ ጂማ በዘንድሮ የበልግ አዝመራ 245 ሺህ 398 ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን ታቅዶ እንደነበር ጠቅሰዋል፡፡
አጠቃላይ ከታቀደውም በ13 ሺህ በላይ ብልጫ በማሳየት 258 ሺህ 671 ሄክታር መሬት በአምስት ዋና ዋና ሰብሎች በዘር ተሸፍኗል፡፡
በልማቱም ከ280 ሺህ የሚበልጡ አርሶ አደሮች መሳተፋቸውን አቶ ቂልጣ አስታውቀዋል።
በዘንድሮ የበልግ አዝመራ ከለማው ከዚሁ መሬት ከ5 ነጥብ 8 ሚሊዮን ኩንታል አጠቃላይ ምርት እንደሚጠበቅ ገልጸዋል፡፡
በጽህፈት ቤቱ የሰብል ልማት ቡድን መሪ አቶ መንግስቱ ሂርባዬ በበኩላቸው፥ ምርታማነትን ለማሳደግ የተመቻቸው አዳዲስ አሰራር የስራ መነሳሳት ፈጥሯል ብለዋል፡፡
ከእነዚህም የኩታ ገጠም፣የመስመርና የትራክተር አስተራረስ ዘዴ የምርጥ ዘርና የተሟላ የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት ዋና ዋናዎቹ እንደሆኑ ጠቅሰዋል፡፡
ለዘንድሮ በልግ ከተዘጋጀው ውስጥ 107 ሺህ ሄክታሩ በመስመር፤ 164 ሺህ ሄክታር መሬት ደግሞ በኩታ ገጠም የአስተራረስ ዘዴ እየለማ ነው ብለዋል፡፡
በልማቱ ከተሳተፉት መካከል የአዶላ ሬዴ፣የዋደራ፣ የሰባቦሩ፣ የግርጃ፣ የአጋ ወዩና ሻኪሶ ወረዳ አርሶ አደሮችም አዳዲሶቹን አሰራሮች በመከተል እያለሙ ይገኛሉ ብለዋል፡፡
በአዳዲስ አሰራር ከለማው ከዚሁ መሬት ውስጥ ከበቆሎ፤ስንዴና ቦለቄ ሰብሎች ከፍተኛ ምርት እንደሚጠበቅ ገልጸዋል፡፡
ለስራው ስኬታማነት ከ95 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያና 37 ሺህ 334 ኩንታል ምርጥ ዘር ጥቅም ላይ መዋሉን አንስተዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025