ወላይታ ሶዶ፤ ግንቦት 25/2017 (ኢዜአ)፡-ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚያከናውኗቸው የጥናትና ምርምር ሥራዎች ሀገራዊ የልማት አቅጣጫን የሚያግዙና ለችግሮች መፍትሄ ጠቋሚ መሆን እንዳለባቸው ተመለከተ።
በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ለኢዜአ ከሰጡ ተመራማሪዎች መካከል የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አባል ፕሮፌሰር ዝናቡ ገብረማርያም እንዳሉት፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚካሄዱ የጥናትና የምርምር ሥራዎች ሀገራዊ የልማት እንቅስቃሴን የሚያሳልጡና ለማህበረሰቡ ችግሮች መፍትሄ ጠቋሚ መሆን አለባቸው።
በተለይ በመንግስት ትኩረት ተሰጥቶ የተለዩ ሀገራዊ የልማት እቅዶችን ለማስፈጸም የሚያግዙ መሆን እንደሚገባቸው ነው የገለጹ።
እንደሀገር ትኩረት በተሰጣቸው የልማት መስኮችና ትኩረቶች ላይ የምርምር ውጤቶች ለመንግስት በማቅረብ በተቀናጀ መንገድ መስራት ይገባል ሲሉም ነው የገለጹት።
የምሁራኑ የምርምር ሥራ የመንግስትን የልማትና የለውጥ ግቦች አቅጣጫ የሚጠቁሙ መሆን ይገባቸዋል ሲሉም ነው የገለጹት።
በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአፈር ምርምርና የእጽዋት ሥነ ምግብ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ሸለመ በየነ በበኩላቸው፣ በዩኒቨርሲቲው የሚካሄዱ የጥናትና ምርምር ሥራዎች ለሀገር እድገት ከፍተኛ ድርሻ እያበረከቱ መሆናቸውን አስታውሰዋል።
የምርምር ውጤቶቹ ልማትን በዘላቂነት ለማጠናከር ካላቸው ፋይዳ በተጨማሪ የአርሶ አደሩን ጊዜ፣ ጉልበትና ወጪን ለመቆጠብ እንዳስቻሉ ገልጸዋል።
በተለይም በአካባቢ ያሉ የልማት አቅሞች በአግባቡ ጥቅም ላይ የሚውሉበትን አማራጭ ማቅረብ ላይ ትኩረት መሰጠት እንዳለበት ነው የገለጹት።
ለምርምር ስራዎች ውጤታማነት ቅንጅታዊ አሰራርን መዘርጋትና ለዘርፉ የተመደበ በጀትን በአግባቡ ሥራ ላይ ማዋል እንደሚገባም ፕሮፌሰር ሸለመ አስገንዝበዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025