የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በክልሉ በበልግ ዝናብና በመስኖ ከለማው ሰብል ከ18 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃል

Jun 3, 2025

IDOPRESS

ደቡብ ቤንች፤ግንቦት 24/2017 (ኢዜአ)፦በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በበልግ ዝናብና በመስኖ ከለማው የአትክልትና ስራስር ሰብሎች ከ18 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።


የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸውን ጨምሮ ሌሎች የስራ ኃላፊዎች በቤንች ሸኮ ዞን ደቡብ ቤንች ወረዳ በኩታ ገጠም እየለማ ያለውን የሽንኩርት ማሳ ተመልክተዋል።


አቶ ማስረሻ በላቸው በወቅቱ እንዳሉት፥ በክልሉ በበልግ ዝናብና በሁለተኛ ዙር መስኖ ከ100 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ ላይ የለማው የአትክልትና ስራስር ሰብል በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል።


ከለማው ማሳም ከ7 ሺህ ሄክታር በላዩ በሽንኩርት የተሸፈነ መሆኑን ተናግረዋል።


በአጠቃላይ በአትክልትና ስራስር ሰብል ከለማው ማሳ 18 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ አመላክተዋል።


በተለይም በደቡብ ቤንች ወረዳ በአርሶ አደር ጓሮ የተጀመረው የሽንኩርት ልማት አሁን ላይ ተስፋፍቶ በኩታ ገጠም መመረት መቻሉ ከአካባቢው አልፎ ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ የሚያስችል እንደሆነም ተናግረዋል።


የቤንች ሸኮ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን በበኩላቸው፥በዞኑ እየተከናወኑ ባሉ የግብርና ስራዎች ውጤት እየታየ ነው ብለዋል።


በደቡብ ቤንች ወረዳ የተጀመረውን የኩታ ገጠም ሽንኩርት ልማት በዞኑ ውስጥ ባሉ ሁሉም ወረዳዎች እንዲስፋፋ ጥረት እንደሚደረግ አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.