ሠመራ፣ግንቦት 26/2017(ኢዜአ)፦በአፋር ክልል የግብርና ግብዓት አጠቃቀም ላይ የታየው መሻሻል መጠናከር እንዳለበት ተመላከተ።
ግብርና ሚኒስቴር በአፋር ክልል የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት፣ አጠቃቀምና ስርጭት ላይ ከክልሉ ባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ መክሯል።
በመድረኩ የተገኙት በግብርና ሚኒስቴር የግብርና ግብዓት አቅርቦት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ መንግስቱ ተስፋ እንዳሉት፥ መንግስት የተለያዩ የግብርና ግብዓቶችን በማቅረብ ምርታማነትን ለማሳደግ እየሠራ ነው።
በዚህም በአፋር ክልል በ2016 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት እንዲጀመር ማስቻሉን ገልጸው፤ አፈፃፀሙም የሚበረታታ መሆኑን ተናግረዋል።
በክልሉ የግብርና ግብዓት አጠቃቀም መሻሻል እየታየ መሆኑን አንስተው፥ ተግባሩ ሊጠናከር እንደሚገባም አመልክተዋል።
መድረኩ የተዘጋጀውም በክልሉ የተሳለጠ የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦትና የግብርና ግብዓት አጠቃቀምን በተመለከተ ለባለድርሻ አካላት ግንዛቤ ለመፍጠር መሆኑንም ጠቁመዋል።
የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሐሩን ዓሊ በበኩላቸው፥ የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት በቅርቡ የተጀመረ ቢሆንም በግብዓትነት መጠቀም ላይ ተስፋ ሰጪ አተገባበር ታይቷል ብለዋል።
በበጀት ዓመቱ በክልሉ በሚገኙ ሰባት ወረዳዎች የአፈር ማዳበሪያ በማቅረብ ላይ እንደሚገኙ የገለፁት ደግሞ በክልሉ የደንከሊያ ግብርና ግብዓት አቅርቦት ህብረት ስራ ዩኒየን ስራ አስኪያጅ አቶ መሰለ ይማም ናቸው።
ለአራት መሠረታዊ ማህበራትና ለኢንቨስተሮች ዩሪያና ዳፕ ማዳበሪያዎችን በማቅረብ ላይ መሆናቸውን ገልፀው፥ እስካሁን 25 ሺህ 995 ኩንታል ማዳበሪያ ማከፋፈላቸውን ገልፀዋል።
የጋሊ ኮማ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ስራ አስኪያጅ ወጣት ሰኢድ ሲራጅ በበኩሉ፥ 1 ሺህ 4 ኩንታል ማዳበሪያ ስርጭት ማከናወኑን ተናግሯል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025