የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የተገኙ ውጤቶች የኢትዮጵያ ማንሰራራት ማሳያ ናቸው

Jun 4, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ግንቦት 26/2017(ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የተገኙ ውጤቶች የኢትዮጵያን ማንሰራራት ማሳያዎች መካከል መሆናቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በአማራ ክልል በጎንደር ከተማ በተካሄደው የ3ኛው “የኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት” ንቅናቄ አካል የሆነ ኤክስፖ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ነው።

በንግግራቸው ጎንደር የትናንት፣ የዛሬና የነገ ሥልጣኔ መገናኛ ከመሆኗም በላይ የአምራች ኢንዱስትሪ ኮሪደር እየሆነች መምጣቷን አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የማንሰራራት ጉዟችን አንዱ ምልክት ነው ብለዋል።

በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የተገኙ ውጤቶች የኢትዮጵያን ማንሰራራት ማሳያዎች መካከል መሆናቸውን የገለጹት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያ በብዙ የምታመርት በትንሹ ደግሞ የምትሸምት ሀገር እንድትሆን እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

የአማራ ክልል በችግር ጊዜም ቢሆን ሰላምን እያሰፈነ የልማት አርበኛ ሆኖ መቀጠል የመቻሉ ህያው ምስክር መሆኑንም ጠቅሰዋል።


በተሳሳተ መንገድ ወደጫካ ታጥቀው የገቡ ልጆቿ የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው እየመጡ ወደ ማህበረሰባቸው እየተቀላቀሉ ይገኛሉ ብለዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ጎንደር እንደ አዲስ እየተወለደች፣ እንደ አዲስ እየተሠራች እንዲሁም እየፈካች መሆኑንም ጠቅሰው፤ ዛሬ በከተማዋ በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍም የተመለከቱት ተግባራትም ይሄንኑ የሚያረጋግጡ መሆናቸውን ገልጸዋል።

መንግሥት ለሰላም እንዲሁም አምራች ኢንዱስትሪውን ጨምሮ ለልማት የሰጠውን ትኩረት አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.