የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ለተረጋጋ የኢኮኖሚ ሥርዓት ግንባታ የንግዱ ማኅበረሰብ ሚና ወሳኝ ነው-ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

Jun 5, 2025

IDOPRESS

ቦንጋ፤ግንቦት 27/2017 (ኢዜአ)፡-ለተረጋጋ ፖለቲካዊ፣ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሥርዓት ግንባታ የንግዱ ማኅበረሰብ ሚና ወሳኝ ነው ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ተናገሩ።

"የብልጽግና ጉዟችንና የንግዱ ማኅበረሰብ ሚና" በሚል መሪ ሀሳብ ክልላዊ የንግዱ ማኅበረሰብ የውይይት መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው።


በመድረኩ ላይ ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) እንዳሉት፥ ለተረጋጋ ፖለቲካዊ፣ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሥርዓት ግንባታ የንግዱ ማኅበረሰብ ሚና ወሳኝ ነው።

በተለይ ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት እንዲመዘገብ ኢንቨስትመንት፣ ኢንዱስትሪ፣የሥራ ዕድል ፈጠራና ማኅበራዊ አገልግሎትን ማጠናር እንደሚገባ ገልጸው፣ለዚህም የንግዱ ማህበረሰብ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

መንግስት የንግዱን ሥርዓት ለማሳለጥና ነጋዴውን ለማበረታታት የተለያዩ ማዕቀፎችን መተግበሩን አጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉም ኢንጂነር ነጋሽ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

የንግዱ ማህበረሰብም ይህን ዕድል በመጠቀም ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት እንዲመዘገብና የተረጋጋ የገበያ ሥርዓት እንዲኖር ሚናውን እንዲወጣም ጠይቀዋል።

መንግስት ጤናማ የንግድ ሥርአትን በመፍጠር ገበያን ለማረጋጋት የሚያደርገውን ጥረት ማገዝ እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በቦንጋ ከተማ የተለያዩ የንግድ ሥራና የልማት እንቅስቃሴዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.