አዲስ አበባ፤ግንቦት 28/2017(ኢዜአ)፦አዲስ አበባ ከተማ የነዋሪዎቿን ህይወት በማሻሻል ረገድ እያስመዘገበች ለምትገኘው ለውጥ የከተማ ግብርና ቁልፍ ምሰሶ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ዛሬ ማምሻውን ከንቲባ አዳነች ከስሎቪንያ ፕሬዝዳንት ናታሳ ፒርክ ሙሳር (ዶ/ር) እና ልዑካቸው ጋር በመሆን ዘመናዊ የንብ ማነብ ሰርቶ ማሳያ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር አካሒደዋል።
በመርሃ-ግብሩ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደገለጹት፥ የንብ ማነብና ከተማ ግብርና ስራ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥና አካባቢን ለመጠበቅ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል።
ብዝሃ ህይወትን ለመጠበቅና የምግብ ሉዓላዊነት የማረጋገጥ ስራ ከአየር ንብረት ለውጥ ስትራቴጂ ጋር የተሰናሰለ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
አዲስ አበባ የጋራ የልማት ግብ ካላቸው ጋር በትብብር እንደምትሰራም ገልጸዋል።
በአዲስ ዙ ፓርክ በይፋ የተጀመረው ዘመናዊ የንብ ማነብ ሰርቶ ማሳያ የአለም አቀፍ ትብብር ማሳያ ጭምር መሆኑን ጠቅሰው፤ ለትምህርትና ለቱሪስት ዘርፍም ጠቃሚ ነው ብለዋል።
የስሎቪንያ ፕሬዝዳንት ናታሳ ፒርክ ሙሳር (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ ሃገራቸው በኢትዮጵያ ዘመናዊ የንብ ማነብ ስራን ለማጠናከር የባለሙያና ቴክኖሎጂ ድጋፍ እንደምታደርግ ገልጸዋል።
አገሪቱ በዘመናዊ ንብ ማነብ ላይ ያላትን ልምድ ለኢትዮጵያ በማጋራት ከዘርፉ የበለጠ ተጠቃሚ ለማድረግ ትሰራለችም ብለዋል።
ስሎቪንያና ኢትዮጵያ መልካም የዲፕሎማሲ ግንኙነት ያላቸው አገራት ናቸው ያሉት ፕሬዝዳንቷ የሀገራቱ ግንኙነት በሌሎች የትብብር መስኮችም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025