አዲስ አበባ፤ ሰኔ 1/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የፕሮጀክቶች ግንባታን በጥራትና በፍጥነት ከማጠናቀቅ አኳያ አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸውን የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ገለጹ፡፡
የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ የተሟላ ማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ አፈጻጸምና በሌሎች ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በማብራሪያቸውም ባለፉት የለውጥ ዓመታት የመንግስት የፕሮጀክቶች አፈጻጸም በፍጥነትና በጥራት በከፍተኛ ደረጃ ማደጉን ተናግረዋል፡፡
በዚህም በመንገድ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም አመርቂ ስራዎች መከናወናቸውን ጠቁመው፤ በአሁኑ ወቅት ከ22ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የመንገድ ፕሮጀክቶች በግንባታ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
በመስኖ ልማት ረገድም የተሻለ አፈጻጸም መመዝገቡን ሚኒስትሩ አንስተው፤ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የቱሪዝም መዳረሻ ልማቶችን በታለመላቸው ጊዜና ጥራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ በዚህም በርካቶቹ ተጠናቀው ወደ አገልግሎት መግባታቸውን ነው የገለጹት፡፡
በተጨማሪም ለማህበራዊ አገልግሎት የሚውሉ የልማት ፕሮጀክቶች አፈጻጸም አመርቂ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡
የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ የውጭ ምንዛሪ ተመን በገበያ መወሰን ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከፖሊሲ ጋር የተገናኙ የኮንትሮባንድ ግፊቶች በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሳቸውን ተናግረዋል፡፡
ማሻሻያውን ተከትሎም በወርቅ ግብይት ላይ የነበረው የኮንትሮባንድ ችግር መፈታቱን ነው የጠቀሱት፡፡
ኢትዮጵያ ከቀጣናው ሀገራት ጋር የምታደርገው የንግድ ግንኙነት፣ የመሠረተ ልማት ትስስርና የኢነርጂ አቅርቦት ተጠናክረው መቀጠላቸውንም አብራርተዋል፡፡
የ2018 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት በቀጣይ ዓመታት የሚኖረውን የማክሮ ኢኮኖሚ ትንበያ ማዕከል ያደረገ፣ የመንግስትን የገቢ አቅም በመተንበይ፣ የሚኖሩ ሌሎች ገቢዎችን ታሳቢ በማድረግና የመንግስትን የወጪ ፍላጎት በመተንተን የተዘጋጀ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
በጀቱ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ማስቀጠል፣ ማህበራዊ ድጎማዎችን እና የተረጋጋ የማክሮ ኢኮኖሚን ከማስቀጠልና ሌሎች ተግባራትን በውጤታማነት ከማከናወን አኳያ ትልቅ ፋይዳ ያለው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በሁሉም አመላካቾች አመርቂ ውጤቶችን እያስመዘገበ መሆኑን ሚኒስትሩ መገልጻቸው ይታወቃል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025