አዲስ አበባ፤ ሰኔ 3/2017(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ውጤታማ መሆኑን የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት አወሉ አብዲ ገለጹ።
ምክትል ፕሬዚዳንቱ በክልሉ የበጀት አመቱ የልማት ፕሮጀክቶች አፈጻጸምን የተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም የክልሉ መንግስት በበጀት አመቱ አስተማማኝ ሰላም ከመገንባት ጎን ለጎን የመሠረተ ልማት ዝርጋታዎችን በስፋት አከናውኗል ብለዋል።
አስተማማኝ ሰላምን ከመገንባት አንጻር ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ በተሰራው ስራ ሰላምና ደህንነት ማረጋገጥ ተችሏል ነው ያሉት።
ለተገኘው ሰላም ህብረተሰቡ ትልቅ ምስጋና እንደሚገባው ጠቅሰው ሰላምን ለማጽናት የሚያግዙ ቀሪ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አመላክተዋል።
በተገኘው ሰላም ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ስራዎችን ቀጣይነት ባለው መልኩ ማከናወን እንደተቻለም ገልጸዋል።
የክልሉ መንግስት የመሠረተ ልማት ስራዎች ወጥነት ባለው መልኩ በጥራትና በፍጥነት እንዲከናወኑ በልዩ ትኩረት ሲሰራ መቆየቱንም ጠቅሰዋል።
በበጀት አመቱ የህብረተሰቡ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሆነው የቆዩ የመንገድ፣ የውሀ፣ የትምህርትና የጤና መሠረት ልማት ስራዎች በስፋት ተከናውነዋል ብለዋል።
በበጀት አመቱ ከ200 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ከ34ሺህ በላይ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ሲከናወኑ መቆየታቸውን አመልክተዋል።
ከፕሮጀክቶቹ መካከል 73 በመቶ የሚሆኑት በህዝብ ተሳትፎ የተከናወኑና ቀሪዎቹ በመንግሥትና በአጋር አካላት የተከናወኑ መሆኑንም አንስተዋል።
አጠቃላይ በግንባታ ላይ ከሚገኙ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች መካካል 27ሺህ የሚሆኑት ግንባታቸው ተጠናቆ ለምረቃ መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።
በክልሉ በህዝብ ተሳትፎ ከተከናወኑ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች መካከል 11ሺህ የመምህራን መኖሪያ ቤቶች፣ 4ሺህ የቅድመ መደበኛ እና 800 የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንደሚገኙበት ጠቅሰዋል።
በተጨማሪም የትምህርት ቤቶች ደረጃ ማሻሻል፣ የህጻናት ማቆያና የህጻናት መጫወቻ ስፍራዎች፣ እንዲሁም የመንገድ ጥገናና የድልድይ ግንባታ ስራዎች በህብረተሰቡ ተሳትፎ የተከናወኑ መሆኑን አመልክተዋል።
በአጠቃላይ የክልሉ መንግስት የጀመራቸው ሰላምን የማጽናት እና ልማትን የማፋጠን ስራዎች የበለጠ ይጠናከራሉ ብለዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025