አዲስ አበባ፤ ሰኔ 3/2017(ኢዜአ)፦በአዲስ አበባ ከተማ የተገነቡ የምርት ግብይት ማዕከላት አምራቹንና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘት የኑሮ ውድነቱን እና የዋጋ ንረትን በመቀነስ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
በአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) የላፍቶ ቁጥር ሁለት ሁለገብ የገበያ ማዕከል ዛሬ መርቀው ስራ አስጀምረዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች የተገነቡ የገበያ ማዕከላት አምራቹንና ሸማቹን እንደ ድልድይ በቀጥታ በማገናኘት የኑሮ ውድነቱን እና የዋጋ ንረትን በመቀነስ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህም ዛሬ የተመረቀው የላፍቶ ቁጥር 2 የገበያ ማዕከልም አምራቹንና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘት የኑሮ ውድነቱን እና የዋጋ ንረትን በመቀነስ የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።
እስካሁን በከተማው በርካታ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳ ያላቸው ፕሮጀክቶች ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ተናግረዋል።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ ህብረተሰቡ ጥራታቸውን የጠበቁ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝና የኑሮ ውድነቱን ለመቀነስ የገበያ መሰረተ ልማቶችን የማስፋት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
የላፍቶ ቁጥር ሁለት ሁለገብ የገበያ ማዕከል በ8 ነጥብ 8 ሄክታር መሬት ላይ የተገነባ ነው።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025