ሀዋሳ፤ ሰኔ 4/2017(ኢዜአ)፦ የሲዳማ ክልል በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ያለውን አቅም መጠቀም የሚያስችል ስራ እያከናወነ መሆኑን የክልሉ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታወቀ።
ቢሮው ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በዘርፉ ላይ ባስጠናቸው የተለያዩ ጥናቶች ላይ ያተኮረ የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።
የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጎሳዬ ጎዳና በዚህ ጊዜ እንደገለጹት ቢሮው በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ያለውን አቅም መጠቀም የሚያስችል በጥናት የተደገፈ ስራ እያከናወነ ነው።
ለዚህም ከ2014 ጀምሮ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የአምራች ኢንዱስትሪ ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀቱን ገልጸዋል።
ፍኖተ ካርታውን ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችል የ10 ዓመት ስትራቴጂክ እቅድና ይህን ተግባራዊ ለማድረግ አቅሞችን ለይቶ የሚሳይ ጥናት መደረጉን አስረድተዋል።
የዛሬው መድረክም ባለድርሻ አካላት ለጥናቶቹ ግብዓት የሚሆኑ ሀሳቦችን እንዲያነሱ የሚያግዝ ነው ብለዋል።
የጥናቱ ዋና ዓላማም አምራች ኢንዱስትሪው በስራ እድል ፈጠራ፣ ተኪ ምርቶችን በማምረት፣ የውጭ ምንዛሬን በማስገኘት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግርና በሌሎች ወሳኝ ዘርፎች የሚያስገኘውን ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ማሳደግ መሆኑንም አመልክተዋል።
በተለይም እንደክልል ያለውን ጠባብ መሬት በተገቢው በመጠቀም ወደ ኢንዱስትሪ ለመሸጋገር የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝ ተናግረዋል።
በመድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ የክልል ቢሮ ኃላፊዎች የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ችሮታው አየለ(ዶ/ር) እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025