አዲስ አበባ፤ ሰኔ 12/2017 (ኢዜአ)፦ በበጀት አመቱ 11 ወራት ከ7 ነጥብ 21 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ከወጪ ንግድ መገኘቱን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 38ኛ መደበኛ ስብሰባ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የ2017 በጀት ዓመት የ11 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ተወያይቷል።
የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) እንደተናገሩት በበጀት አመቱ በሀገሪቱ የወጪ ንግድ ታሪክ ከፍተኛ የሆነ ገቢ ተገኝቷል።
ከጠቅላላ የወጪ ንግድ 4 ነጥብ 59 ቢሊየን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን አስታውሰው በአፈጻጸም ከእቅድ በላይ 7 ነጥብ 21 ቢሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን ገልጸዋል።
በበጀት አመቱ መጨረሻ ከ 8 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅም ጠቁመዋል።
በበጀት አመቱ 11 ወራት ከወጪ ንግድ የተገኘው ገቢ ከ2016 በጀት አመት ጋር ሲነጻጸር ከ 3 ነጥብ 96 ቢሊየን ዶላር በላይ ጭማሪ ማሳየቱንም ጠቅሰዋል።
በማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ ከተሳኩ ኢኮኖሚያዊ ውጤቶች መካከል የወጪ ንግድ ዘርፍ ከፍተኛ አፈጻጸም እየተመዘገበበት መሆኑንም አክለዋል።
በወጪ ንግድ ምቹ ምህዳር መፈጠሩ፣ የተለያዩ የህግና አሰራር ማነቆዎች መፈታታቸው፣ ከላኪዎች እና ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በተሻለ ቅንጅት በመሰራቱ በአገሪቱ ታሪክ ከፍተኛውን ገቢ ማግኘት ተችሏል ብለዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025