አዲስ አበባ፤ ሰኔ 12/2017(ኢዜአ)፦ የስራ ባህልን በትውልድ ውስጥ ለማስረጽ የሃይማኖት ተቋማት፣ ትምህርት ቤቶች፣ መገናኛ ብዙሃንን ጨምሮ የባለድርሻ አካላት ሚና የላቀ ሊሆን እንደሚገባ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ።
"የስራ ባህል ምርታማነት ለሀገር ሉዓላዊነት" በሚል መሪ ሃሳብ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የፓናል ውይይት ተካሂዷል፡፡
በውይይቱ ማጠቃለያ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል እንዳሉት የስራ ባህል ግንባታ ስኬታማ እንዲሆን ትውልድን ከታች ጀምሮ መቅረጽ ይገባል፡፡
ትውልድን በመቅረጽ የሃይማኖት ተቋማት፣ ትምህርት ቤቶች፣ መገናኛ ብዙሃንን ጨምሮ የባለድርሻ አካላት ሚና የላቀ ሊሆን እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ለሙያ ያለን አመለካከት የአስተሳሰብ ለውጥ የሚፈልግ ነው ያሉት ሚኒስትሯ ከቤተሰብ ጀምሮ የስራ ባህልን ማዳበር እንደሚያስፈልግ ጠቅሰዋል፡፡
ያሉንን አቅምና ጸጋ መለየት በዛ ላይ ተመስርቶ ፈጠራና ፍጥነትን በማከል ውጤታማ ስራ ማከናወን ይጠበቅብናል ነው ያሉት፡፡
በዚህ ረገድ እንደሀገር መልካም ጅምሮች በመኖራቸው ይህንኑ በማስፋት ለውጤት እንዲበቃ ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡
ምርታማነትን ማሳደግ በሚያስችሉ የቴክኖሎጂና የሰው ሃይል ልማት ላይ ይበልጥ መስራት እንደሚገባ ተነስቷል፡፡
እንደ ኮሪደር ልማትና ህዳሴ ግድብ ያሉ መልካም ተሞክሮዎችን ማስፋት እንደሚገባም ነው የተገለጸው፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025