የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የባህር በር ለኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

Jun 20, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 12/2017(ኢዜአ)፦ የባህር በር ለኢትዮጵያ የፖለቲካ አጀንዳ ሳይሆን የህልውናዋ ጉዳይ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከመላው ኢትዮጵያ ከተውጣጡ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጋር ውይይት አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የኢትዮጵያ የሁልጊዜም ፍላጎት ከጎረቤቶቿ ጋር በጋራ መልማት መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ሰላም መሆንና መልማት ለቀጣናው ዕድገት በጎ ሚና እንደሚጫወትም ጨምረው ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር እና ከፍተኛ የህዝብ ብዛት አላት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰላም እና ልማት ለኢትዮጵያ ቁልፍ ጉዳዮች እንደሆኑ ጎረቤቶቿ ሊረዱ እንደሚገባ አመልክተዋል።


ኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄዋ በህጋዊ እና ሰላማዊ መንገድ ምላሽ እንዲያገኝ እየሰራች እንደምትገኝም ተናግረዋል።

የባህር በር ጉዳይ የፖለቲካ አጀንዳ አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዳዩ ለኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይ ነው ብለዋል።

የባህር በር አለመኖር በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ እንደሚገኝ ገልጸው ጉዳዩ አፈጣኝ መፍትሄ እንደሚያሻው አመልክተዋል።


ኢትዮጵያ የባህር በር እንደሚፈያስፈልጋት እና ይህም በንግድ ህጎች አማካኝነት ምላሽ ያገኛል ብለው እንደሚያምኑም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

የጎረቤት ሀገራት የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ በቀናነት እንዲረዱትና ጥያቄው ከመልማት እና ከማደግ ካለ ጽኑ ፍላጎት የመነጨ እንደሆነ መገንዘብ እንደሚገባቸው አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.