ሰመራ፤ ሰኔ 12/2017(ኢዜአ)፦ በአፋር ክልል አምራች ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያጎለብቱ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ አስታወቁ።
በአፋር ክልል በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የተገነቡ አምራች ኢንዱስትሪዎች ተመርቀው ወደ ስራ እየገቡ ነው።
ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በሎጊያ ከተማ በ159 ሚሊየን ብር የተገነቡ የተፈጥሮ ምንጭ ውሃና የዱቄት ፋብሪካዎችን ዛሬ መርቀው ስራ አስጀምረዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ እንደገለፁት በክልሉ አምራች ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ ገብተው የስራ ዕድል መፍጠር እንዲችሉ እየተሰራ ነው።
አሁን ላይ ወደ ስራ እየገቡ ያሉት ፋብሪካዎች የስራ ዕድልን ከመፍጠራቸው ባሻገር የስራ ባህል እንዲያድግ አስተዋፅኦ እያደረጉ ነው ብለዋል።
አምራች ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያጎለብቱ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑንም ነው የተናገሩት።
የክልሉ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ኤይሻ ያሲን በበኩላቸው በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አማካኝነት በርካታ ኢንዱስትሪዎች ወደ ማምረት መግባታቸውን ገልጸዋል።
በዚህ ዓመት ይመረቃሉ ተብለው በዕቅድ ከተያዙት አስር ፋብሪካዎች መካከል ስድስቱ ለአገልግሎት መብቃታቸውን ገልጸው ቀሪዎቹ በቀጣይ ወራት ውስጥ ተመርቀው ለአገልግሎት ይበቃሉ ብለዋል።
ዛሬ ከተመረቁት ፋብሪካዎች መካከል 'አዋሽ' የማዕድን ውሃ ፋብሪካ ባለቤት እና ስራ አስኪያጅ ኢብራሂም ሰኢድ፤ ፋብሪካው በ119 ሚለየን ብር መገንባቱን ገልጸዋል።
ፋብሪካው ለ150 ሰዎች የስራ ዕድል የፈጠረ መሆኑንም ጨምረው ተናግረዋል።
የሉሲ ዱቄት ፋብሪካ ባለቤትና ስራ አስኪያጅ ኢብራሂም መሐመድ ሰኢድ በበኩላቸው ፋብሪካው በ40 ሚሊየን ብር መገንባቱን ጠቅሰው በቀን 260 ኩንታል ዱቄት የማምረት አቅም አለው ብለዋል።
ለአካባቢው ነዋሪዎች የስራ ዕድል መፍጠሩን ጠቁመው በቀጣይነት የመኮረኒና ፓስታ ፋብሪካ ለማስፋት ዕቅድ እንዳላቸው ገልጸዋል።
በፋብሪካው በተፈጠረልኝ የስራ ዕድል ራሴንና ቤተሰቤን መጥቀም ችያለሁ ያሉት ደግሞ የሎጊያ ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ ፋጡማ አብደላ ናቸው።
በምረቃ ስነ-ስር'ቱ ላይ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና የሎጊያ ከተማ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025