የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በክልሉ የመንግሥት የፋይናንስና የንብረት አስተዳደርን በዲጂታል ቴክኖሎጂና ቀልጣፋ አሰራር የታገዘ ማድረግ ተችሏል

Jun 23, 2025

IDOPRESS

ጅግጅጋ፤ ሰኔ 13/2017(ኢዜአ)፦ በክልሉ የመንግሥት የፋይናንስና የንብረት አስተዳደርን በዲጂታል ቴክኖሎጂና ቀልጣፋ አሰራር የታገዘ መሆኑን የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ አስታወቀ።

ከሀገራዊ ለውጡ በኋላ በሶማሌ ክልል ያለውን የመንግሥት የፋይናንስና የንብረት አስተዳደር አሰራርን በተመለከተ የክልሉ የፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ ደይብ አህመድኑር ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም የፋይናንስ አስተዳደር ማሻሻያ ስራ በትክክል ለውጥ ያመጣ እና ውጤትም የተመዘገበበት መሆኑን አብራርተዋል።

የበጀት አስተዳደር አዋጅ እና ለተፈጻሚነቱ የሚያገለግሉ 10 የህግ ማቀፎች ተዘጋጅተው በመተግበር ላይ መሆናቸውን አንስተዋል።

የመንግሥትን የፋይናንስና የንብረት አስተዳደር ስርዓት በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ እየተደረገ መሆኑንና በዚህም የላቀ ውጤት መምጣቱን ተናግረዋል።

የመንግሥት ፋይናንስና የንብረት የመረጃ አያያዝ በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ ዘመናዊ አሰራርን እየተከተለ መሆኑንም ገልጸዋል።

ከሰባት አመታት በፊት የክልሉ በጀት 15 ቢልዮን ብር እንደነበር አስታውሰው አሁን ላይ 41 ቢልዮን ብር መድረሱን አስታውቀዋል።

ከበጀቱም 60 በመቶው ለድህነት ቅነሳ የሚያገለግሉ የልማት ስራዎች ላይ እየዋለ መሆኑን ጨምረው አስረድተዋል።

በክልሉ የገቢ መሰብሰብ አቅምም ከለውጡ በፊት ከነበረበት ከ12 በመቶ ከፍተኛ እድገት አሳይቶ አሁን ላይ 43 በመቶ ደርሷል ብለዋል።

የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች የሆኑ የልማት ድርጅቶች ኢንተርፕራይዞች እና የበጎ አድራጎት ድርጅቶች በጀት አስተዳዳር አዋጅ ተግባራዊ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑንም አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.