ጎንደር፤ ሰኔ 14/2017(ኢዜአ)፡- በጎንደር ከተማ እየተጠናቀቀ ባለው በጀት ዓመት ከአንድ ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ብር በላይ ግብር መሰብሰብ መቻሉን የከተማ አስተዳደሩ ገቢዎች መምሪያ አስታወቀ።
የደረጃ "ሐ" ግብር ከፋዮች ከመጪው ሐምሌ ጀምሮ በዲጂታል ስርዓት ግብራቸውን የሚከፍሉበት አሰራር ለመተግበር የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ዛሬ ተካሂዷል።
የመምሪያው ሃላፊ ወይዘሮ ጥሩዬ አታክልት በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ የከተማው የንግድ እንቅስቃሴ የሚያመነጨውን ገቢ በመሰብሰብ ለልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች ለማዋል ትኩረት ተሰጥቶ ሲሰራ ቆይቷል።
በዚህም በጀት ዓመት እስካሁን ከአንድ ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ብር በላይ ግብር በመሰብሰብ ለከተማዋ ልማት መፋጠን ማዋል መቻሉን አስታወቀዋል።
የተሰበሰበው ገቢም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ350 ሚሊዮን ብር ብልጫ ያለው መሆኑን አስረድተዋል።
ለገቢው ማደግም በበጀት ዓመቱ ከሁለት ሺህ በላይ አዳዲስ ግብር ከፋዮች ወደ ግብር መረቡ እንዲቀላቀሉ መደረጉ አስተዋጽኦው ከፍ ያለ ነው ብለዋል።
የገቢ አሰባሰቡን ለማሻሻልም ዲጅታላይዜሽንን እስከ ታች ድረስ በመተግበር ለግብር ከፋዩ ከቀድሞ የተሻለ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በሐምሌ 2017 ዓ.ም ጀምሮ የደረጃ "ሐ" ግብር ከፋዮች ባሉበት ሆነው በዲጂታል የግብር ክፍያ ስርዓት የሚጠበቅባቸውን ግብር እንዲከፍሉ ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ አንሰተዋል።
በዲጂታል የግብር ክፍያ ስርዓቱ ከ14ሺ በላይ የደረጃ "ሐ " ግብር ከፋዮች መካተታቸውን ጠቁመው፤ የግብር ከፋዮች መረጃዎችንም ዲጂታላይዝ የማድረግ ስራዎች መከናወናቸውን አስረድተዋል።
በከተማው የልማት ስራዎችን በማጠናቀቅ የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የግብር አሰባሰቡን ማዘመን እንደሚገባ የገለጹት ደግሞ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማ አስተዳደሩ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ሃላፊ አቶ ግርማይ ልጃለም ናቸው።
በከተማው የሰፈነው ሠላም በርካታ የልማት እቅዶችን ለማከናወን ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ጠቁመው፤ የግብር ክፍያ ስርዓቱን ለማዘመን የተጀመሩ የዲጂታል ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።
በጎንደር የአዘዞ ጠዳ ክፍለ ከተማ ገቢዎች ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ደስታው ሙሉነህ፤ ዲጂታል የግብር ክፍያ ስርዓት የመንግስትን ግብር አሟጦ ለመሰብሰብ ምቹ መደላደል የሚፈጥር ነው ብለዋል።
በመድረኩ በየደረጃው የሚገኙ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች፣ የገቢ ተቋሙ ባለሙያዎችና አጋር አካላት ተሳትፈዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025