
ወላይታ ሶዶ፤ ሰኔ 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመረጃዎችን ጥራትና ተዓማኒነት ለማሳደግ የተቀናጀ የመረጃ አስተዳደር ስርዓትን ማጠናከር እንደሚገባ ተመላከተ።
በክልሉ የተቀናጀ የመረጃ አስተዳደር ስርዓትን ለማሳደግ ያለመ መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በመድረኩ የተገኙት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የወላይታ ሶዶ ክላስተር አስተባባሪ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ተፈሪ አባተ ለሁለንተናዊ ዕድገት የመረጃ አያያዝን ማዘመን አስገዳጅ መሆኑን ተናግረዋል።

ለተግባራዊነቱም የክልሉ መንግስት መረጃን የመሰብሰብ፣ የመተንተን እና የማደራጀት ስራዎችን ለማዘመን በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
መረጃን በአግባቡ ሰብስቦ ጥቅም ላይ በማዋል የህዝብን ፍትሃዊ ተጠቃሚነትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄን ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን ያነሱት ደግሞ የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍቃደ ስላሴ ቤዛ ናቸዉ።
የክልሉን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና መልክዓ ምድራዊ የልማት መረጃዎችን በጥራት በመሰብሰብ በአግባቡ ሰንዶ ለመያዝ ጥረት መደረጉንም አስረድተዋል።

የተሰበሰቡና የተተነተኑ መረጃዎች በዳታ ቤዝ ቋት ተደራጅተው ለማስቀመጥ የተሰሩ ተግባራትን ለማጠናክር መድረኩ መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡
የመረጃዎችን ጥራትና ተዓማኒነት ለመጠበቅ የተቀናጀ የመረጃ አስተዳደር ስርዓትና ቋት ማዘጋጀት አስፈላጊ ነው ብለዋል።
ይህም መረጃ ለተመራማሪዎች፤ ለፖሊሲ አውጭዎችና ለውሳኔ ሰጭ አካላት ተደራሽ አንዲሆን በቴክኖሎጂ መደገፉን ተናግረዋል፡፡
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስነ-ህዝብ ልማት ፈንድ ፕሮግራም አስተባባሪ ወይዘሮ ገዙ ብርሃኑ በበኩላቸው ጥራቱን የጠበቀና ወቅታዊ መረጃን መሰብሰብ ለሀገር ዕድገት ወሳኝ መሆኑን አስረድተዋል ።
በዚህም ረገድ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የሀገር ውስጥ ስታቲስቲክስ መረጃዎችን በመሰብሰብ በማቀነባበር እና ተንትኖ ለተጠቃሚዎች በማቅረብ ረገድ ከፕሮግራሙ ጋር በጋራ መስራቱን ተናግረዋል።

ፕሮግራሙ መረጃን በማመንጨትና ለተጠቃሚዎች ለማቅረብ ከሚደረጉ ጥረቶች አንፃር የህዝብና ቤት ቆጠራ፣ የስነ ህዝብ ጤና ጥናት እንዲሁም ሌሎችንም እንደሚደግፍ አመልክተዋል።
በመድረኩም የክልል፣ የዞን እና የከተማ አስተዳደሮች ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።
አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...
Sep 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...
Aug 31, 2026
ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...
Aug 17, 2026
ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...
Jul 27, 2026