አዲስ አበባ፤ሰኔ 17/2017(ኢዜአ)፦በፌደራል የመንግሥት መስሪያ ቤቶች 32 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ያልተሰበሰበ ሂሳብ መኖሩን የፌደራል ዋና ኦዲተር መሰረት ዳምጤ ተናገሩ።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 39ኛ መደበኛ ስብሰባው የፌዴራል ዋና ኦዲተር የፌዴራል መንግሥት መስሪያ ቤቶች የ2016 በጀት ዓመት ሒሳብ የፋይናንሺያል፣ የሕጋዊነት እና የክዋኔ ኦዲት ሪፖርትን አዳምጧል።
የፌደራል ዋና ኦዲተር መሰረት ዳምጤ ባለበጀት መስሪያ ቤቶች የመንግስትን ህግና መመሪያ ተከትለው በጀትን ስለመጠቀማቸው የተከናወነውን የኦዲት ሪፖርት ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።
በፌደራል የመንግሥት የክፍያ መመሪያ መሰረት ለውሎ አበልና ለመጓጓዣ የተሰጠ ቅድሚያ ክፍያ ሰራተኛው ሥራውን አጠናቆ ከተመለሰ በኋላ በሰባት ቀናት ውስጥ መወራረድ እንዳለበት ያስቀምጣል።
በተመሳሳይ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በሒሳብ አያያዝ መመሪያ መሰረት ደግሞ ለሥራ ማስኬጃ የተሰጠ ቅድሚያ ክፍያ በሰባት ቀናት ውስጥ መወራረድ እንዳለበት ያስቀምጣል፡፡
በዚህም በ137 መሥሪያ ቤቶችና በ20 የገቢዎችና ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ላይ የተሰብሳቢ ሂሳብ ደንብና መመሪያን ተከትለው መፈጸማቸውን ለማረጋገጥ ኦዲት መደረጉን አብራርተዋል።
በዚህም በአጠቃላይ 32 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር በወቅቱ ያልተወራረደ ወይንም ያልተሰበሰበ ሂሳብ መኖሩ በኦዲት መረጋገጡን በሪፖርታቸው አመላክተዋል፡፡
ይህ ሂሳብ መወራረድ ከነበረበት ጊዜ ከአንድ ወር እስከ አስር አመት የቆየ መሆኑንም ዋና ኦዲተሯ አመላክተዋል።
በመሆኑም ውዝፍ ተሰብሳቢ ሂሳብ በወቅቱ እንዲወራረድ አለማድረግ የመንግሥትን ገንዘብ የሚያባክን በመሆኑ በአስቸኳይ መወራረድ እንዳለበት ማሳሰቢያ መሰጠቱን ጠቁመዋል።
ለረጅም ዓመታት ሳይሰበሰቡ የተገኙ ሂሳቦች እንዲወራረዱ አስፈላጊው ክትትል እንዲደረግ፣ ሊሰበሰቡ የማይችሉትን በመንግሥት መመሪያ መሠረት ከመዝገብ እንዲሰረዙ ለተቋማቱ ማሳሰቢያ መላኩንም ገልጸዋል፡፡
በተመሳሳይ ያልተሰበሰበ ውዝፍ የገቢ ሂሳብ፣ ገቢ ያልተደረገ የጉዳት ካሳ፣ ማስረጃ ሳይቀርብ በወጪ የተመዘገቡና ትክክለኛነቱን ለማረጋገጥ ያልተቻለ ሂሳብና ሌሎች የኦዲት ሪፖርቶችን አቅርበዋል።
ደንብና መመሪያን ያልተከተለ የወጪ ሂሳብ፣ የግዥ አዋጅ ደንብና መመሪያን ያልተከተለ ግዥ መፈጸምና ሌሎች የኦዲት ግኝቶችም ቀርበዋል።
በመንግስት የግዥ አዋጅ ደንብና መመሪያ መሰረት ግዥ መፈጸማቸውን ለማረጋገጥ በ70 መስሪያ ቤቶችና በሰባት ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች በተደረገ ኦዲት ከ 404 ሚሊዮን ብር በላይ መመሪያውን ያልተከተለ ግዥ መፈጸሙ ተረጋግጧል ብለዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025