ሮቤ፤ ሰኔ 19/2017 (ኢዜአ ) በባሌ ዞን የልማት ፕሮጀክቶችን በተሻለ ፍጥነትና ጥራት በማጠናቀቅ ለህብረተሰቡ ተጠቃሚነት እንዲውሉ እየተደረገ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዱልሀኪም አልይ ገለጹ።
የክልሉ እና የዞኑ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በባሌ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ 160 የልማት ፕሮጀክቶችን የማስመረቁ ሂደት እንደቀጠለ ነው።
በዛሬው ዕለትም በጎባና ዲንሾ ወረዳዎች ተገንብተው ለአገልግሎት የበቁ የ''ቡኡረ ቦሩ'' የተሰኘ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ማብለያ ማዕከል፣ ድልድይ፣ የገጠር መንገድና ሌሎች ፕሮጀክቶች ተመርቀዋል።
የባሌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዱልሀኪም አልይ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፣ በዞኑ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን በተሻለ ፍጥነትና ጥራት በማጠናቀቅ ለህብረተሰቡ ተጠቃሚነት እንዲውሉ እየተደረገ ነው።
በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ተገንብተው ለአገልግሎት የበቁት 160 የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች የዚሁ ጥረት አካል መሆናቸውን ተናግረዋል።
በተለይ ፕሮጀክቶቹ የአርሶ አደሩን የትምህርት ተደራሽነትና ጤናውን በማሻሻል በኩል አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ በመሆናቸው ልዩ ያደርጋቸዋል ብለዋል።
እንዲሁም አርሶ አደሩ ምርቱን በቀላሉ ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚነቱ ይበልጥ እንዲረጋገጥ የሚያግዙ የገጠር መንገድና የድልድይ ግንባታ እንደሚገኝበት አክለዋል።
በምረቃ መርሓ ግብሩ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ መስኖና አርብቶ አደር ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሮባ ቱርጬ በበኩላቸው የክልሉ መንግሥት ከለውጡ ማግስት ጀምሮ የህዝቡን የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ እየመለሰ ነው።
በተለይ የልማት ፕሮጀክቶቹ የህዝብን የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ከመመለስ ባሻገር ተጠቃሚነቱን ይበልጥ ማሳደግ እንዲችሉ ታስቦ የተገነቡ መሆናቸውንም አመልክተዋል።
መንግስት የህብረተሰቡን ህይወት ለመለወጥ የሚያደርገው ጥረት እንዲሳካ ህዝቡም የአካባቢውን ሰላምና ደህንነት ይበልጥ መጠበቅና ለልማት ፕሮጀክቶቹ እንክብካቤ እንዲያደርግም አቶ ሮባ ጠይቀዋል።
በወረዳው የህብረተሰቡ የረዥም ጊዜ ጥያቄ የነበሩ 24 የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ከ65 ሚሊዮን ብር ወጪ ተገንብተው ለአገልግሎት መብቃታቸውን የገለጹት ደግሞ የጎባ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አብዱልቃድር ኡስማን ናቸው።
ከወረዳው ነዎሪዎች መካከል አቶ ሁሴን አህመድ በሰጡት አስተያየት የፕሮጀክቶቹ መገንባት መንግስት ለህዝቡ የገባውን ቃል ጊዜውን ጠብቆ እንደሚመልስ ማሳያዎች ናቸው ብለዋል።
በተለይ የቅድመ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቱ ግንባታ ልጆቻቸው ከአካባቢያቸው ሳይርቁ የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ስለሚያደርግ በሂደቱ የተሳተፉ አካላትን አመስግነዋል።
በባሌ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ የተገነቡ ፕሮጀክቶችን የማስመረቁ ሂደት እንደሚቀጥል ከመርሐ ግብሩ ለመረዳት ተችሏል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025