አዲስ አበባ ፤ ሰኔ 22/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ የውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በምስራቅ አፍሪካ የስልጠና ልህቀት ማዕከል ለመሆን የሚያስችል የአቅም ግንባታ እና ሎጂስቲክስ የማሟላት ስራ እያከናወነ መሆኑን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ የውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ታመነ ሀይሉ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት፤ የአቅም ግንባታ ስራ ኢንስቲትዩቱ ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል አንደኛው ነው።
ኢንስቲትዩቱ በዘርፉ ያለውን ችግር በመለየት ስልጠና እየሰጠ መሆኑንና እስካሁን ባለው ከ18 አገራት ለተውጣጡ ከ200 በላይ ባለሙያዎች ስልጠና መስጠቱን ተናግረዋል።
ኢንስቲትዩቱ በዘርፉ የምስራቅ አፍሪካ የስልጠና ልህቀት ማዕከል የመሆን ርዕይውን ለማሳካት እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
ኢንስቲትዩቱ በዘርፉ ያሉ ችግሮችን በጥናት በመለየት መፍትሄ ከማበጀት ባለፈ ዘመናዊ ላቦራቶሪ እየገነባ መሆኑንም ነው የገለጹት።
በውሃ ዘርፍ ላይ ስልጠና ለሚሰጡ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ጠቁመው በአመት የሚያሰለጥናቸው ባለሙያዎች ቁጥር እያደገ መምጣቱንም አብራርተዋል።
ኢንስቲትዩቱ ከ10 አመት በፊት በአመት 150 የሚጠጉ ባለሙያዎችን ያሰለጥን እንደነበር አንስተው አሁን ላይ ከ2ሺህ በላይ ሰልጣኞችን በአመት እየተቀበለ መሆኑን ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ የውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አገልግሎቱን በማስፋት ዘርፉ የሚፈልገውን ድጋፍ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
የኢንስቲትዩቱ ላቦራቶሪ አለም አቀፍ እውቅና ለማግኘት ሰነድ መዘጋጀቱን ገልፀው፤ የልህቀት ማዕከል ለመሆን የሚያስችለውን ስራ እያከናወነ ነውም ብለዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025