🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2018(ኢዜአ)፡- የአዲስ አበባ የተርሚናል ኢንተርፕራይዝ ማኅበራት የተሳለጠ የትራንስፖርት ፍሰት እንዲፈጠር እያደረጉ እንደሚገኝ የከተማ አስተዳደሩ የትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ።
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ያብባል አዲስ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የነዋሪዎችን የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የአቅርቦት ፍላጎት ለማሳለጥ የተሻለ የአሰራር ሥርዓት እየተፈጠረ ነው።
የመንገድ ደኅንነትና የትራፊክ መጨናነቅን ለመቀነስም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ከዚህ በፊት የታክሲ ተራ አስከባሪ በመባል የሚታወቀውን አደረጃጀት በአዲስ መልክ በተደራጀው የተርሚናል ኢንተርፕራይዝ አማካኝነት የተሻለ የትራንስፖርት አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን አንስተዋል።
በተርሚናል ኢንተርፕራይዝ የተደራጁ አስተባባሪዎችም የትራፊክ መጨናነቅና የተሳፋሪዎችን እንግልት በመቀነስ የተሳለጠ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ በመፍጠር ጉልህ ፋይዳ እያበረከቱ መሆኑን ገልጸዋል።
በአዲሱ የትራንስፖርት አስተባባሪዎች የተርሚናል ኢንተርፕራይዝም ግልጽና የአሰራር ሥርዓትን በተከተለ አግባብ በ87 ማኅበራት በማደራጀት የተሻለ አገልግሎት የሚሰጡበት ሁኔታ መፈጠሩን አስረድተዋል።
በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ አማካኝነት በአዲስ በተዋቀረው የተርሚናል ኢንተርፕራይዝ የተደራጁ አስተባባሪዎችም የክህሎት ስልጠና ተሰጥቷቸው ወደስራ እንዲሰማሩ መደረጉን ገልጸው፤ የሚሰበስቡት ገንዘብ ዘመናዊ የአሰራር ሥርዓትን የተከተለ መሆኑን ተናግረዋል።
የኢንተርፕራይዝ ማኅበራት አባላቱም ለሁለት ዓመታት በሚኖራቸው ቆይታ ዕድገት ተኮር በሆኑ ዘርፎች የሚሸጋገሩበት የቁጠባ ሥርዓት መዘርጋቱን አብራርተዋል።
በመዲናዋ የተደራጁ የተርሚናል ኢንተርፕራይዝ ማኅበራትም የነዋሪዎችን የትራንስፖርት አገልግሎት በማሳለጥ ምቹ የትራፊክ ፍሰት በመፍጠር አዎንታዊ ሚና እየተወጡ መሆኑን ገልጸዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025