🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ መስከረም 29/2018 (ኢዜአ)፦ ዘላቂ የገቢ እድገትን ለማረጋገጥና የዘርፉን ችግር ለመፍታት የሪፎርም ስራዎችን ማጠናከርና በጋራ መስራት እንደሚገባ የገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ ገለጹ።
የገቢዎች ሚኒስቴር ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ከሀገራዊ የገቢ ዘርፍና ቁልፍ ከሆኑ የፌዴራል፣ የክልልና የከተማ አስተዳደር ባለድርሻ አካላት ጋራ ሀገራዊ ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

በውይይቱ ሚኒስቴሩ አመራር አባላት፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮችና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ሲሆን፤ መድረኩ በ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀምና በ2018 በጀት ዓመት እቅድ ላይ የሚመከርበት መሆኑ ተገልጿል።
በፊዚካል ፌዴራሊዝም ፖሊሲ አፈፃፀምና በገቢ ግብር አዋጅ አተገባበር ላይ መግባባት የሚደረስበት መድረክ ነው ተብሏል።
በዚሁ ወቅት የገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል።
ባለፉት የለውጥ ዓመታት የገቢ ዘርፍ የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖረው ለግብር ከፋዩ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል።
ለታክስ ህግ ተገዢ ህብረተሰብ ለመፍጠርና የታክስ ህግን አውቆ የሚያስተገብር የሰው ኃይል ለመገንባት የተጀመረውን ሪፎርም ከፌዴራል እስከ ክልል በወጥነት መተግበር እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።
በዚህም የ2018 በጀት ዓመት ሀገራዊ የገቢ እቅድን በማሳካት ዘላቂ የገቢ እድገትን ለማረጋገጥና የዘርፉን ችግር ለመፍታት በጋራ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።
የፌዴራልና የክልል የገቢ ተቋማት በህገ ወጥ ንግድ ላይ ተገቢውን ክትትል ማድረግና ከሚመለከታቸው የህግ አስከባሪ ተቋማት ጋር በቅንጅት መስራት አለባቸው ብለዋል።
ከታክስ መረቡ ውጪና በታክስ መረቡ ውስጥ ሆነው ህገ ወጥ ተግባር የሚፈፅሙትን ስርዓት ማስያዝና የዜጎችን ሞራል መገንባት እንደሚጠበቅም አብራርተዋል።
ኢኮኖሚዊው የሚያመነጨውን ገቢ መሰብሰብ አገራዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን አንስተው፤ የአገር ውስጥ ሀብት የማሰባሰብ ስራን አጠናክሮ መተግበር እንደሚገባም ተናግረዋል።
በገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ስርዓት ማጣጣምና የክልሎች ድጋፍ ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ አበበ በበኩላቸው፤ በገቢ ዘርፉ በተደረገው ሪፎርም ሀገር አቀፍ የገቢ አፈፃፀምን ማሳደግ መቻሉን ተናግረዋል።
በዚህም የገቢ አፈፃፀም በ2011 በጀት ዓመት ከነበረበት 277 ቢሊዮን ብር በላይ በ2017 ወደ አንድ ነጥብ አራት ትሪሊዮን ብር ማሳደግ መቻሉን አስታውቀዋል።
በ2018 በጀት አመት የታቀደውን ከሁለት ትሪሊየን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ በዘርፉ የሚታዩ የአሰራርና የቅንጅት ችግሮችን በትብብር መፍታተ ይገባል ብለዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025