🔇Unmute
አምቦ፤ ጥቅምት 1/2018(ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን በ7 ሺህ 437 ሄክታር መሬት ላይ አትክልትና ፍራፍሬ እየለማ መሆኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ባለሙያ አቶ መንገዱ ጉርሙ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በዞኑ ለአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ትኩረት ተሰጥቶ ስራው እየተከናወነ ይገኛል።

በክረምቱ ወራትም በተከናወነ የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ስራ የተሻለ ምርት ለማግኘት የሰብል እንክብካቤ እና ጥበቃ እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።
በዚህ ወቅትም በ7 ሺህ 437 ሄክታር መሬት ላይ ምርጥ የአቮካዶ ዝርያዎች፣ ማንጎ፣ አፕል፣ ፓፓያና ሙዝ እየለማ መሆኑን ገልጸዋል።
በተጨማሪም ብርቱካን፣ ሎሚና ዘይቱን እንዲሁም ሌሎች የአትክልት አይነቶች እየለሙ መሆኑን ጠቅሰው በአጠቃላይ በአትክልትና ፍራፍሬዎች እየለማ ከሚገኘው መሬት 646 ሺህ ኩንታል ምርት ለማግኘት መታቀዱን ተናግረዋል።

የታቀደውን ምርት ለማግኘት የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት ከወረዳ እስከ ቀበሌ ድረስ የግብርና ባለሙያዎችን መድቦ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አውስተዋል።
በአትክልትና ፍራፍሬ እየለማ ከሚገኘው መሬት ውስጥ አንድ ሺህ 353 ሔክታር መሬት በኩታ ገጠም የለማ መሆኑን ገልጸዋል።

አትክልትና ፍራፍሬ በብዛት እየለማ ያለባቸው ወረዳዎች ዳኖ፣ ኖኖ፣ ቶኬ ኩታዬ፣ ምዳቀኝ፣ ግንደበረት፣ ሊባን ጃዊ እና ጅባት ወረዳዎች እንደሆኑም ገልጸዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025