🔇Unmute
ደብረ ማርቆስ ፤ ጥቅምት 1/2018(ኢዜአ)፡- በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ አሟጦ በመሰብሰብ ለልማት የሚውለውን ወጪ በራስ አቅም ለመሸፈን ጥረት እየተደረገ መሆኑን የከተማው አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ አስታወቀ።
መምሪያው የ2018 የመጀመሪያው ሩብ ዓመቱን የእቅድ አፈጻጸም የግምገማ መድረክ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ዛሬ አካሂዷል።
በመድረኩ ላይ የመምሪያው ኃላፊ ጌታቸው አለበል እንደገለጹት፤በከተማ አስተደደሩ ከሚካሄደው የንግድ እንቅስቃሴ ገቢን አሟጦ በመሰብሰብ ለልማት ለማዋል በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።
በዚህም በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ብቻ ከ306 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ በመሰብሰብ በከተማዋ ለሚካሄዱ የልማት ስራዎች ማዋል መቻሉን አንስተዋል።
የተሰበሰበው ገቢም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 30 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ብልጫ እንዳለው አብራርተዋል።
በከተማው ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ አሟጦ በመሰብሰብ የልማት ወጪን በራስ አቅም ለመሸፈን እየተደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉም ተመልክቷል።

የዛሬው የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ዓላማም በግብር አሰባሰቡ ላይ የታዩ ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል እና ክፍተቶችን ለይቶ በማረም በቀጣይ የተሻለ ለመፈጸም መሆኑ ተጠቁሟል።
በከተማዋ የመንቆረር ክፍለ ከተማ የግብር ባለሙያ ስመኘው ውቤ በበኩላቸው፤ ግምገማው ድክመትና ጥንካሬን በግልጽ ያሳየ በመሆኑ ለቀጣይ ስራችን ውጤታማነት ተነሳሽነትን ፈጥሮልናል ብለዋል።
በተለይም ለግብር ከፋዩ ማህበረሰብ ስለግብር አስፈላጊነትና ሰርቶ ባገኘው ልክ አሳውቆ እንዲከፍል ተከታታይ ትምህርት ለመስጠት የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።
ሌላኛው የዘርፉ ባለሙያ ያለም ዳኘ፤ የከተማዋን እድገት በማፋጠን የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የገቢ አሰባሰብ ስራን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።
በግምገማ መድረኩ ላይ የመምሪያው፣ የክፍለ ከተሞችና የየቀበሌዎች የገቢ ሰብሳቢ አመራሮችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025