የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ሕብረተሰቡ በማኅበራዊ መተግበሪያዎች ከሚደርሱ መጭበርበሮች እራሱን እንዲጠብቅ ተጠየቀ

Oct 17, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 6/2018 (ኢዜአ)፡- በማኅበራዊ የመገናኛ መተግበሪያዎች አማካኝነት የማጭበርበር ወንጀሎች ፈጽመዋል የተባሉ አካላት በሕግ እንዲጠየቁ እየሠራ መሆኑን የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ።

አንዳንድ በማጭበርበር ድርጊት ላይ የተሰማሩ ሰዎች ከግለሰቦች ዕውቅና እና ፈቃድ ውጭ በሞባይሎቻቸው ውስጥ በመግባት የግለሰቦቹን የማኅበራዊ መገናኛ መተግበሪያዎች (እንደ ዋትስአፕ እና ቴሌግራም የመሳሰሉትን) ምስጢራዊ መረጃዎች በመስረቅ የገንዘብ ማጭበርበር ድርጊት ላይ መሰማራታቸውን አገልግሎቱ ገልጿል።

ግለሰቦቹ የማኅበራዊ መገናኛ መተግበሪያዎችን ከተቆጣጠሩ በኋላ እውነተኛ የአካውንት ባለቤት በመምሰል በግለሰቦቹ ስልኮች ተመዝግበው ለሚገኙ ቤተሰቦች፣ ዘመዶች፣ ጓደኞች፣ እና የሥራ ባልደረቦች ገንዘብ እንደተቸገሩ የሚገልፅ የጽሑፍ መልዕክት በመላክ ለዚሁ የማጭበርበር ዓላማ ወደ ተዘጋጀ የባንክ አካውንት እንዲላክላቸው ያደርጋሉ ብሏል፡፡

የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት የደረሱትን ጥቆማዎችን መሰረት በማድረግ በወንጀል ድርጊቱ ላይ የተሳተፉ አካላትን በመለየት እና በመከታተል በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ከሚመለከታቸው ባለ ድርሻ ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሠራ መሆኑን ለኢዜአ በላከው መረጃ አስታውቋል።

ሕብረተሰቡም ይህን የማጭበርበር ድርጊት ለመከላከል ወደ ስልኩ ለሚደርሱ መልዕክቶች ምላሽ ከመስጠቱ አስቀድሞ በተለያዩ መንገዶች የመልዕክቱን ትክክለኛነት በማረጋገጥ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል።

እንዲሁም ከሚመለከታቸው ተቋማት የሚተላለፉ የጥንቃቄ መልዕክቶችን በመከታተል ራሱን ከወንጀል ድርጊቶች እንዲጠብቅ እና ወንጀል ተፈፅሞ ሲገኝም ለሕግ አስከባሪ አካላት እንዲያሳውቅ ጥሪ አቅርቧል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.