የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የዋጋ ንረትን በመቀነስ ገበያውን ማረጋጋት ተችሏል

Oct 27, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ጥቅምት 16/2018 (ኢዜአ)፡-ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ባለፉት ሦስት ወራት በቂ የግብርናና ኢንዱስትሪ ምርቶች እንዲቀርቡ በማድረግ ገበያውን ማረጋጋት መቻሉን አስታወቀ።

የግብርናው ዘርፍ ምርታማነት እንዲያድግ መንግሥት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ያለው ሥራ በቂ አቅርቦት እንዲኖር ማስቻሉን እና የገበያ ዋጋን በማረጋጋት ሂደት በጎ ሚና ማበርከቱን በሚኒስቴሩ የሀገር ውስጥ ንግድ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሊቁ በነበሩ ተናግረዋል።

እንዲሁም መንግሥት በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ባንኮች ለዘርፉ ተዋንያኖች በቂ ምንዛሪ በማቅረባቸው ስኳርና የምግብ ዘይት በስፋት ለገበያ እንዲቀርብ አስችሏል ብለዋል።

በዚሁ መሠረት 1 ሚሊየን 677 ሺህ 934 ኩንታል ስኳር እና 198 ሚሊየን 949 ሺህ 288 ሊትር የምግብ ዘይት በነፃ ገበያው በኩል ለሸማቹ መቅረቡን ለኢዜአ ተናግረዋል።

በተጨማሪም 311 ሺህ ኩንታል ስኳርና 2 ሚሊየን ሊትር ዘይት በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አማካኝነት ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች በተመጣጣኝ ዋጋ መሠራጨቱን ነው ያረጋገጡት።

በቀጣይም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት የምርት አቅርቦትን በማሳደግ ገበያውን የማረጋጋቱ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።

በሌላ በኩል የቅዳሜና እሁድ ገበያዎችን ለማስፋት በተከናወነ ሥራ 71 አዳዲስ ገበያዎች መከፈታቸውን ጠቅሰው፤እስካሁንም 1 ሺህ 638 የሰንበት ገበያዎች አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን አስታውቀዋል።

በእነዚህ ገበያዎች በተፈጠረ የገበያ ትስስርም 1 ሚሊየን 86 ሺህ 419 ኩንታል የኢንዱስትሪ፣ 6 ሚሊየን 219 ሺህ 77 ኩንታል አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም 2 ሚሊየን 93 ሺህ 120 ኩንታል የሰብል ምርቶች ግብይት መፈጸሙን ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.