የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የኮሪደር ልማት የፈጠራ ዐቅምና የኑሮ ዘዬ ለውጥ እያመጣ ነው -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Oct 29, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ጥቅምት 18/2018 (ኢዜአ)፡-የኮሪደር ልማት ሥራችን ከፍተኛ የፈጠራ ዐቅም እና የኑሮ ዘዬ ለውጥ እያመጣ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ከኮሪደር ልማት ጋር በተያያዘ በሰጡት ማብራሪያም፤ ከፍተኛ የአመለካከት ለውጥ የመጣበት ሥራ መሆኑን በአጽንኦት ገልጸዋል።

ሰው ከልማዱ ጋር ለመፋታት ቢቸገርም በሂደት አዲሱን ዓለም ይቀበላል፤ ስለዚህ ሥራችንን እናጠናክራለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የኮሪደር ልማት ሥራችን ከፍተኛ የፈጠራ ዐቅም እና የኑሮ ዘዬ ለውጥ እያመጣ ነው ብለዋል።

የኮሪደር ልማት ሥራው ብዙ ዐቅሞች እንዲወጡ ማስቻሉን ጠቁመው፤ለምሳሌ ከወንዝ ዳርቻዎች ልማት ጋር በተያያዘ የውጭ ሰዎች ከብዷቸው የተውትን የሀገራችን ሰዎች በብቃት እየሠሩት መሆኑን በአድናቆት አንስተዋል።

ከስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ሥራ ጋር በተያያዘም በአዲስ አበባ ብቻ ከ1 ሺህ በላይ አነስተኛ ስታዲየሞች ገንብተናል ብለዋል።

ይህ ማለትም ወጣቶችን ከጫት እና ከሽሻ ላይ ተሻምተን ወደ ኳስ ሜዳ እያስገባናቸው ነው ማለት ነው ሲሉ አብራርተዋል።

ዜጎችን ከድራፍት ቤት ተሻምተን ወደ ኳስ ሜዳ እያስገባን ነው፤በጋራ የእግር እንቅስቃሴ በማድረግ የቤተሰብ ቁርኝት እንዲያድግ አስችለናል።

የሚታይ ከተማ እየፈጠርን ነው፤እግር ኳስ ሜዳዎቹ በመጪዎቹ 10 ዓመታት ለብሔራዊ ቡድን ቁልፍ ተጫዋቾችን ለማፍራት ያግዛሉ።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.