🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 18/2018(ኢዜአ)፦ ትግራይ ልማት ያስፈልጋታል በመሆኑም በሰላማዊ መንገድ በትብብር ለልማት መስራት ይገባል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አስገነዘቡ።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትግራይ ክልል ያለውን የሰላም ሁኔታ በሚመለከት በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ ትግራይ ልማት ያስፈልጋታል በመሆኑም በሰላማዊ መንገድ በትብብር ለልማት መስራት ይገባል ብለዋል።
በትግራይ ክልል ተጨማሪ ወጊያ እንዲካሄድ አንፈልግም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚያ ይልቅ ተባብረን ሀገር ማልማት ነው የምንፈልገው ነው ያሉት።
ከዚያ ውጭ መንግስትን በሃይል ለመጣል ፍላጎት ካለ እሱ ፈጽሞ ሊሳካ አይችልም የፌደራል መንግስት ለትግራይ ክልል የሚመድበው በጀት ለልማት ሳይሆን ለታጣቂ እየዋለ ነው ሲሉም ገልጸዋል።
ይህ ትክክል እንዳልሆነ ጠቁመውም ትግራይ ልማት ያስፈልጋታል በመሆኑም በሰላማዊ መንገድ በትብብር ለልማት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025