🔇Unmute
አሶሳ፤ ጥቅምት 20/2018(ኢዜአ)፦ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ይፋ የተደረጉ የጉባ ላይ ብስራቶች ኢትዮጵያን በአፍሪካ የግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት የሚያደርጉ መሆናቸውን በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሃብት መምህርና ተመራማሪው ሙሐመድ ኢብራሂም ተናገሩ።
በአፍሪካ ግዙፍ የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከ14 ዓመታት የግንባታ ሂደት በኋላ ተጠናቆ በይፋ ተመርቆ ለአገለግሎት መብቃቱ ይታወቃል።
የዚህ ግድብ መጠናቀቅ በቀጣናው የኃይል ትስስር ለመፍጠርና የኢትዮጵያን ማንሰራራት እውን የሚያደረግ ስለመሆኑም ተነስቷል።
በመሆኑም የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅን ተከትሎ የኢትዮጵያን እድገትና ማንሰራራት ዘላቂ ለማድረግና የሀገሪቷን የወደፊት እጣ ፋንታ የሚወስኑ የተለያዩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ግንባታ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጉባ ላይ ይፋ መደረጋቸው ይታወሳል።
በጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፋ የተደረጉት የጉባ ላይ ብስራቶች ምን ትርጉም አላቸው ሲል ኢዜአ በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሃብት መምህርና ተመራማሪ የሆኑትን ሙሐመድ ኢብራሂምን አነጋግሯል።
መምህሩ በማብራሪያቸው የመንግስት የልማት ጥረቶች በሀገር ላይ መሰረታዊ ለውጦችን ማምጣት የሚችሉ እና የኢትዮጵያን ማንሰራራት የሚያስቀጥሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የጉባ ላይ ብስራቶች ኢትዮጵያን በአፍሪካ የግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት የሚያደርጉ የእድገትና ብልጽግና ማረጋገጫ ሁነኛ መገለጫዎች ናቸው ሲሉም አብራርተዋል።
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከግብርና መር ተላቆ ብዝሃ ዘርፎችን ማእከል አድርጎ እየተሰራበት በመሆኑ መሰረታዊ ለውጥ እየታየበት መሆኑንም አንስተዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በሀገሪቷ የተከናወኑ እና በሂደት ላይ ያሉ እንዲሁም በእቅድ የተያዙ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን የወደፊት እጣ ፈንታ የሚወስኑ ናቸው ብለዋል።
በኢትዮጵያ የፕሮጀክቶች ግንባታ ሂደት ፍጥነትን፣ ጥራትንና ብቃትን አጣምሮ የመፈፀም አቅም በተግባር እየታየ በመሆኑ የሚፈለገው ሀገራዊ ስኬት እድገትና ብልጽግና እውን የሚሆንበት ጊዜ ብዙም ሩቅ ሊሆን እንደማይችል ተናግረዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፋ የተደረጉት የጉባ ላይ ብስራቶች የማዳበሪያ ፋብሪካ፣ የኒውክሌር ግንባታ ፕላንት፣ ግዙፉ የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ፣ የ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ቤቶች ግንባታና የጋዝ ልማትን ጨምሮ በድምሩ የ30 ቢሊዮን ብር ፕሮጀክቶች መሆናቸው ይታወቃል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025