የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር የሁለትዮሽ የገበያ ድርድር ተፈራረመች

Nov 6, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 26/2018(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት የድርድር አባልነት ድርድር አካል የሆነውንና ሦስተኛውን የሁለትዮሽ የገበያ ድርድር ከቻይና ጋር በማጠናቀቅ በጄኔቫ ተፈራርማለች።

ፊርማውን በተባበሩት መንግሥታት እና ጄኔቫ በሚገኙ ሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የኢትዮጵያ አምባሳደር እና ቋሚ ተወካይ አምባሳደር ፀጋአብ ክበበውና በዓለም ንግድ ድርጅት የቻይና አምባሳደር እና ቋሚ ተወካይ ሊ ዮንግጂ ፈርመውታል።

እዚህ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ የተደረሰው ሀገራቱ መካከል ውጤታማ ውይይቶችና ቴክኒካል ድርድሮች ከተደረጉ በኋላ መሆኑም ተጠቁሟል።

ይህም የኢኮኖሚ ትብብርን ለማጠናከር፣ ፍትሐዊ፣ ሁሉን አቀፍ እና ሕጎችን መሠረት ያደረገ ዓለም አቀፍ የንግድ ሥርዓትን ለማንበር ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳያል ተብሏል።

የዓለም ንግድ ድርጅት የድርድር አባልነት ድርድር አካል የሆነውን ይህን የሁለትዮሽ የገበያ ድርድር ኢትዮጵያ ቀደም ሲል ከቱርክዬ እና አርጀንቲና ጋር መፈራረሟ ይታወቃል።

በቀጣይም ከሌሎች ሀገራት ጋር ተመሳሳይ ድርድሮችን በማጠናቀቅ መፈራረም የሚያስችሉ ሥራዎች በትኩረት እየተከናወኑ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.