🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 27/2018(ኢዜአ)፦የቻይና-አፍሪካ በጋራ ተጠቃሚነት መርህ የተመሰረተ ስትራቴጂክ አጋርነት የአህጉሪቷን የመሠረተ ልማት ክፍተት በመሙላት ገንቢ ሚና እየተወጣ እንደሚገኝ የአፍሪካ ኢምፖርት-ኤክስፖርት ባንክ (አፍሪኤግዚም ባንክ) አስታወቀ።
‘’ቻይና ለአፍሪካ ኢንዱስትሪ፣ ለአረንጓዴና ዘላቂ ልማት ድጋፍ ታደርጋለች’’ በሚል መሪ ሀሳብ በቻይና የአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ እና የውይይት የጥናትና ትብብር ማዕከል ከፐልስ ኦፍ አፍሪካ ሚዲያ (POA) ጋር በመተባበር የተዘጋጀ የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

በቻይና የኢንዱስትሪና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የኢንዱስትሪ ፖሊሲና ደንቦች ዋና ዳይሬክተር ሊ ሊየጁን፤ የቻይና አፍሪካ ልማት በሥነ-ምኅዳር ተስማሚ የልማት መስክ የተመሠረተ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም በፈረንጆቹ 2025 ዓመትም በቻይና አፍሪካ የጋራ ትብብር የአህጉሪቷን የታዳሽ ኃይል ሽግግር የሚያፋጥን ከ1 ነጥብ 5 ጊጋ ዋት በላይ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል ብለዋል።
በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሠረተው የቻይና አፍሪካ አጋርነትም በኢንዱስትሪ፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሽግግር መስክም በስትራቴጂክ የልማት ዕቅድ ተጠናክሮ መቀጠሉን አስረድተዋል።

የቻይና አፍሪካ የኢኮኖሚ ትብብርን ታሳቢ በማድረግ የአህጉሪቷን ምርታማነት በማሻሻል በኢንዱስትሪ ዕሴት ሰንሰለት የንግድ ልውውጥ ላይ ትኩረት መሰጠቱን አስረድተዋል።
በአፍሪካ የሀገር ውስጥ የኢንዱስትሪ ፓርኮች እና በቻይና ከፍተኛ የቴክኖሎጂ የኢንዱስትሪ ልማት ፓርኮች መካከል የተቀናጀ ልማት ትብብር ምኅዳር መፈጠሩንም አብራርተዋል።
በአፍሪካ ኢምፖርት-ኤክስፖርት ባንክ የባንክ ኦፕሬሽኖች ዳይሬክተር ክዋቤና አዪሬቢ (ዶ/ር)፤ ቻይና በተሻጋሪ ስትራቴጂክ ዕቅድ በአጭር ጊዜ ዕድገትን ያስመዘገበች ሀገር ናት ብለዋል።
የቻይና አፍሪካ የልማት ትብብር ድኅነትን በማስቀረት አህጉሪቷ በግዙፍ መሰረተ ልማት፣ በሰው ሃብት ልማትና አህጉራዊ ውህደት ፕሮጀክቶች ዕድገት በማገዝ ጉልህ ፋይዳ እንዳላት ገልጸዋል።

ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታትም ቻይና የአፍሪካ የንግድ አጋር ብቻ ሳትሆን የኢንዱስትሪ፣ የአረንጓዴና ዘላቂ ልማት ርዕይ ስኬት ወሳኝ አጋር መሆኗን ተናግረዋል።
በቻይና 'ቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ' የአፍሪካን ኢኮኖሚ የዕሴት ሰንሰለቶች የሚያሳልጥ የትራንስፖርት፣ ወደቦችና የኃይል መሠረተ ልማት ትስስር ኢንቨስትመንት መጠናከሩን አንስተዋል።
በኢትዮጵያ በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች የስራ ዕድል ከፈጠረው የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ እስከ ዘላቂ ዕድገትን በሚያጎለብቱ የደቡብ አፍሪካ የንፋስ ኃይል ፕሮጀክት ድረስ የቻይና የ50 ቢሊየን የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትና ብድር የአፍሪካን የመሠረተ ልማት ክፍተት እየሞላ ነው ብለዋል።
በቀጣይም በጋራ ተጠቃሚነት መርህ የተመሰረተው የቻይና አፍሪካ ግንኙነትም የጋራ ብልጽግናን ለማሳለጥ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በቻይና ብሔራዊ የልማትና ማሻሻያ ኮሚሽን የዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ ምርምር ተቋም የክፍል ዳይሬክተር ዩዋን ሸንግሎንግ (ዶ/ር)፤ በመጪው ዘመን በቻይና-አፍሪካ ማህበረሰብ መካከል የጋራ ዕድልን የመገንባት ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

የቻይና-አፍሪካ ስትራቴጂና ዕቅድ ትብብርም በፖሊሲ በኢንዱስትሪ፣ በቴክኖሎጂ፣ በመሠረተ ልማት፣ በፋይናንስ ድጋፍ ቁልፍ አቅጣጫዎች ተመሰረተ መሆኑን ገልጸዋል።
የቻይና-አፍሪካ የልማት ስትራቴጂና ዕቅድ ትብብርም በጋራ ጥረት ላይ የተመሰረተ ጠንካራ ግንኙነትና የጋራ ዕድገትን የሚጠይቅ የረጅም ጊዜ ተግባር መሆኑን አስገንዝበዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025