🔇Unmute
ሆሳዕና ፤ጥቅምት 28/2018 (ኢዜአ) ፡-የገጠር ኮሪደር ልማት ስራው የአኗኗር ዘይቤያቸውን በመቀየር የተሻለ ህይወትን እንዲመሩ እንዳደረጋቸው በሀዲያ ዞን የሌሞ ወረዳ አርሶ አደሮች ተናገሩ፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት ወደ ተግባር የገባው የገጠር ኮሪደር ልማት በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ተግባራዊ እየሆነ ይገኛል።
ይህም አርሶ አደሩ የአኗኗር ዘይቤውን በመቀየር የተሻለ ህይወት እንዲመራ በማድረግ መሰረታዊ ለውጥ እንዲመጣ ምቹ መደላድል እየፈጠረ እንደሚገኝ እየታየ ነው።
የገጠር ኮሪደር ልማት እሳቤው ምቹና ጽዱ አካባቢን ከመፍጠር ባለፈ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚደረግ ጥረት እንዲጠናከር በማድረግ ረገድ ጉልህ አበርክቶ ያለውና ተጨባጭ ለውጦችንም እያስመዘገበ እንዳለ ይነገራል።
የገጠር ኮሪደር ልማት በተጠናከረ መልኩ እየተተገበረባቸው ከሚገኙ አካባቢዎች መካከል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀዲያ ዞን ሌሞ ወረዳ አንዱ ሲሆን የዞኑ አርሶ አደሮች ልማቱ የአኗኗር ዘይቤያቸውን በመቀየር የተሻለ ህይወት እንዲመሩ እንዳደረጋቸው ለኢዜአ ተናግረዋል።
አስተያየታቸውን ከሰጡት ውስጥ በወረዳው የዱባንቾ ቀበሌ ነዋሪው አርሶ አደር ጳውሎስ ኃይለማርያም እንደገለፁት፤የገጠር ኮሪደር ልማት ትግበራ የቀደመ የአኗኗር ዘይቤያችንን በመሰረታዊነት እንዲቀየር ምቹ ሁኔታ ፈጥሮልናል፡፡
በዚህም ልማቱ አካባቢያቸውን ጽዱና ለኑሮ ምቹ በማድረግ በተሻለ ከባቢ የመኖር ባህል እንድንላመድ አድርጎናል ያሉት አርሶ አደሩ የማሳ አጠቃቀምና አመራረት ዘይቤያችንም እንዲንቀየር እያደረገ ነው ብለዋል፡፡
ሌላኛዋ የዚሁ ቀበሌ ነዋሪና የገጠር ኮሪደር ልማቱ ተጠቃሚ የሆኑት ወይዘሮ ነፃነት ወርቁ በበኩላቸው፤ ልማቱ ከዚህ ቀደም ምግብ ለማብሰል እንጨት በመልቀም ህይወትን ይመሩበት የነበረውን ልማድ በዘመናዊ አኗኗር እንዲቀየር ማድረጉን ገልፀዋል።
ያለውን ማሳ በአግባቡ መጠቀም እንዲችሉ ያደረጋቸው ሲሆን የአትክልትና ፍራፍሬ ተክሎችን በቅርበት በማግኘት የተመጣጠነ ምግብ ከጓሮቸው በማግኘት ልጆቻቸው በአዕምሮ እንዲበለፅጉ ምቹ ሁኔታ እየተፈጠረ ስለመምጣቱም ተናግረዋል፡፡
የገጠር ኮሪደር ትግበራው ዘመናዊ የአኗኗር ዘይቤን እንዲያጣጥሙ ከማድረግ በተጨማሪ ለግብርና ስራቸው ውጤታማነት ዘርፈ ብዙ እድል ይዞላቸው እንደመጣ የተናገሩት ደግሞ አርሶ አደር ደሳለኝ ደፋር ናቸው፡፡
ከዚህ ቀደም ሰውና እንስሳት በአንድ ላይ ይኖሩ ስለነበር ንፅህናውን ያልጠበቀ ህይወት ይመሩ እንደነበር አስታውሰው የገጠር ኮሪደር ልማቱ ይህንን ሁኔታ በመቀየር ዘመናዊ ኑሮ እንድንኖር አስችሎናል ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ ዞንን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የገጠር ኮሪደር ልማት አካል የሆነው ሞዴል የገጠር መንደሮች በቅርቡ መመረቃቸው ይታወሳል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025