የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እንግልትን በማስቀረት ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት እንድናገኝ አስችሎናል-ተገልጋዮች   

Nov 13, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

ሆሳዕና ፤ ህዳር 3/2018(ኢዜአ)፦ የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እንግልትን በማስቀረት ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት እንድናገኝ አስችሎናል ሲሉ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሆሳዕና ማዕከል ተገልጋዮች ገለጹ፡፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ መሶብ የአንድ ማእከል አገልግሎት መስከረም 15 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ ሥራ መጀመሩ ይታወቃል።


የማዕከሉን የሥራ እንቅስቃሴ በተመለከተ የኢዜአ ሪፖርተር በስፍራው በመገኘት ተገልጋዮችና የሚመለከታቸውን የሥራ ሃላፊዎች አነጋግሯል።

ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል አቶ ዳንኤል በየነ፣ አቶ ደስታ ኤርቻዮ እና አቶ ደመቀ ሙሉነህ ፤ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት እንግልትን በማስቀረት ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለማግኘት እንዳስቻላቸው ተናግረዋል።

አገልግሎቱ በአንድ ማዕከል በርካታ ጉዳዮችን ጨርሶ መውጣት ከማስቻሉ ባለፈ ፈጣን፣ ቀልጣፋ፣ ጊዜና ገንዘብ ቆጣቢ መሆኑንም ተናግረዋል።

በመሆኑም መሰል የአገልግሎት ማዕከላትን በማስፋት በተገልጋዮች ላይ ሲደርስ የነበረን እንግልት እና የብልሹ አሰራር መንስኤዎችን ማስቀረት አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል።


የማዕከሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ከበደ ሻሜቦ፤ በማዕከሉ የተለያዩ ተቋማት 20 አገልግሎቶች እየተሰጡ መሆኑን ገልጸው በቀጣይ በማዕከሉ የሚሰጡ አገልግሎቶች እየሰፋ ይሄዳሉ ብለዋል።

በማዕከሉ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ከመስጠት ባለፈ ብልሹ አሰራሮችን ለማስቀረት እያስቻለ በመሆኑ በተጠናከረ መልኩ ይቀጥላል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.