የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በምእራብ ሸዋ ዞን ከ466 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ እየለማ ነው

Nov 13, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አምቦ ፤ ህዳር 3/2018 (ኢዜአ)፡-በምእራብ ሸዋ ዞን በዘንድሮ የበጋ ወራት 466 ሺህ 750 ሄክታር መሬት በመስኖ እየለማ መሆኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

በጽህፈት ቤቱ የአትክልት ባለሙያ አቶ መላኩ ተፈራ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በዞኑ የከርሰ ምድርና የገፀ ምድር የውሃ ሃብትን በመጠቀም የመስኖ ልማት ስራት በስፋት የማከናወን ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል።


በመስኖ እና የግብርና ግብዓት አጠቃቀም እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ስራዎች ላይ ለአምራቾች ግንዛቤ በመስጠት ወደ ስራ እንዲገቡ መደረጉን ተናግረዋል።

በዚህም መሰረት በዘንድሮው ዓመት በዞኑ ከ400 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ለማልማት ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

በእስካሁኑ ሂደትም ከ70 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ስንዴን ጨምሮ በተለያዩ ሰብሎች ስለመሸፈኑ ጠቅሰው እቅዱን ለማሳካት የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።


በዚህ ዓመት በሁለት ዙሮች ከሚካሄደው በበጋ መስኖ ልማት ከ26 ነጥብ5 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱንም ተናግረዋል፡፡

በዞኑ ባለፈው ዓመት በአንደኛና በሁለተኛ ዙር በመስኖ ከለማ መሬት 25 ሚሊዮን ኩንታል ምርት መገኘቱን ከጽህፈት ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.