🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ህዳር 10/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ የኢንተርፕርነርሽፕ ስልጠናዎች ችግር ፈቺ የፈጠራ ውጤትና መፍትሔ እያስገኙ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰለሞን ሶካ ገለጹ፡፡
የኢንተርፕረነርሽፕ ልማት ኢንስቲትዩት ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጀውን ዓለም አቀፍ የኢንተርፕርነርሽፕ ሳምንት በማስመልከት የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።
ዓለም አቀፍ የኢንተርፕርነርሺፕ ሳምንት የዘርፉ ተዋንያን ንቁና ብቁ ተሳትፎ በማድረግ ችግር ፈቺ የፈጠራ ውጤቶች ላይ ትኩረት አድርገው እንዲሰሩ ለማበረታታት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
በዚሁ ጊዜ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰለሞን ሶካ፤ መንግስት የኢትዮጵያን የኢንተርፕርነርሽፕ ምኅዳር ለማስፋት በከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
ባለፉት ሰባት ዓመታትም የኢንተርፕርነርሽፕ ሥነ-ምህዳሩን ማስፋት የሚያስችሉ የአሰራርና የተቋማት የሪፎርም አጀንዳ በመቅረጽ ወሳኝ ስራ መሰራቱን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ኢንተርፕርነሪያል መንግስት ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ይህም ከባህላዊ የአሰራር ሥረዓት ጠባቂነት በመላቀቅ ንቁ፣ ችግር ፈቺ እና ዕድል ፈጣሪ መሆን እያስቻሉት መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህም መንግስት ውጤታማ የመፍጠንና መፍጠር የአገልግሎት ሥርዓትን በመዘርጋት ስኬት እየተመዘገበ እንደሚገኝ አንስተዋል።
የመንግስትን የአሰራር ስርዓት በፈጠራ የታገዘ እንዲሆን የፐብሊክ ሰርቪስ ኢኖቬሽን ላቦራቶሪ በማቋቋም አገልግሎቶችን የማሳለጥ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የኢንተርፕርነርሽፕ ልማት ኢንስቲትዩት ከተቋቋመ ጀምሮም የኢንተርፕርነር ስልጠና አቅሞችን በማሳደግ በአንድ ጊዜ በርካታ ዜጎችን የማሰልጠን አቅም እየዳበረ መምጣቱን አስረድተዋል።
ኢትዮጵያውያን ኢንተርፕርነሮችን በዓለም አቀፍ ውድድሮች ብቁና ንቁ ተወዳዳሪ በማድረግ ሀገራቸውን ከድህነት የሚያወጡ ዜጎችን ማፍራት እንደሚያስችል ገልጸዋል፡፡
በሌላ በኩል ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የኢንተርፕርነርሽፕ ማህበረሰብ አካል እንድትሆንም የኢንተርፕርነርሽፕ ልማት ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን አንስተዋል።
በዚህም ባለፈው ዓመት በተደረገው ዓለም አቀፍ የኢንተርፕርነርሽፕ ሳምንት ውድድር ላይ ኢትዮጵያ በ8ኛ ደረጃ ማጠናቀቅ አንዳስቻላት አስታውሰዋል።
በኢትዮጵያ የኢንተርፕርነር ስልጠናዎች ችግር ፈቺ የፈጠራ ውጤትና መፍትሔ እያስገኙ መሆኑን ነው የተናገሩት።
የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የኢንተርፕርነርሺፕ ሳምንት የፈጠራ አቅሞችን ማጎልበት የሚያስችል መድረክ ነው ብለዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025