የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ኢትዮጵያ ያላትን ዕምቅ አቅም በመጠቀም በላቀ የኢኮኖሚ ዕድገት እየተጓዘች ነው 

Nov 20, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ሕዳር 10/2018 (ኢዜአ)፡-ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ያላትን ዕምቅ አቅም በመጠቀም በላቀ የኢኮኖሚ ዕድገት እየተጓዘች ነው ሲሉ የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሴሪ አንዋር ኢብራሂም ገለጹ።

የኢትዮጵያ ማሌዢያ ከፍተኛ የቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል በተካሄደው ፎረም ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር)፣ የኢንቨስትመንት ኮሚሸን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር)ን ጨምሮ የሀገራቱ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የንግድና ኢንቨስትመንት አልሚ ባለሀብቶች ተገኝተዋል።


የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሴሪ አንዋር ኢብራሂም፤ ኢትዮጵያ በአፍሪካና በዓለም ውስጥ አድናቆት የተቸራት ታላቅ ሀገር መሆኗን እንደሚያውቁ ገልጸዋል።

ለዚህም ነብዩ መሐመድ ወደ ሐበሾች ምድር የላኳቸውን የመጀመሪያ ሙስሊም ስደተኞች የክርስቲያን ንጉስ በፍቅርና አክብሮት እንደተቀበላቸው አስታውሰዋል።

ይህ ዓይነቱ ታሪክም በመረዳዳትና ዕውቀት ላይ የተመሰረተ ግንኙነትን በመፍጠር የጋራ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ወሳኝ ትምህርት መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮ-ማሌዢያን ግንኙነት ይበልጥ በማጠናከር የጋራ ትብብሮችን ማስፋት እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል።

የዲጂታል ሽግግር፣ የዳታ ዘርፍ እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት መሠረታዊ የኢኮኖሚ ማሳለጫ የመፍትሔ መንገዶች መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያም ባለፉት ዓመታት ያላትን ዕምቅ አቅም በመጠቀም በላቀ የኢኮኖሚ ዕድገት እየተጓዘች መሆኗን ጠቁመው፤ ይህም የሚበረታታ መሆኑን አንስተዋል።


የማሌዢያ የፖለቲካዊ መረጋጋት ከኢንዱስትሪ ማስተር ፕላን እስከ የኢነርጂ ሽግግር፣ የመንገድ ካርታ እስከ ዲጂታል ሽግግር ስትራቴጂና መሠረተ ልማት ግንባታ ድረስ በወጪ ንግድ ጠንካራ ሀገር መሆኗን አስረድተዋል።

የማሌዢያ የንግዱ ማህበረሰብ ልዑካን ተሳትፎ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ግንኙነታችንን ለማጠናከር ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ነው ብለዋል።

የሀገራቱን ትብብርም እንደትልቅ ዕድል በመጠቀም በጋራ መስራት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

በኢትዮጵያ አዲስ አበባ ለተደረገላቸው የላቀ የእንግዳ አቀባበል ደማቅ ሥነ-ስርዓት ምስጋና አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.