🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 10/2018(ኢዜአ)፦ በ1920ዎቹ ከኢትዮጵያ የተወሰዱ 12 ውድ ቅርሶችን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናት እና ምርምር ተቋም ተቀብሏል።
ቅርሶቹ የፕሮፌሰር ራሞን አያት እንዲሁም በ1920ዎቹ በኢትዮጵያ የጀርመን ልዑክ በነበሩት ፍራንዝ ዊስ የአገልግሎት ዘመን ከኢትዮጵያ የተወሰዱ ሲሆን፣ ፍራንዝ እና ባለቤታቸው ሄድዊግ ገንዘብ ከፍለው የሰበሰቧቸው ናቸው።

ለዩኒቨርሲቲው ከተበረከቱት ውድ ቅርሶች ውስጥ ዘውድ፣ ጋሻ፣ ጎራዴ፣ ዝናር፣ ስዕሎች እንዲሁም ከራስ ተፈሪ መኮንን የተበረከቱ ስጦታዎች ይገኙባቸዋል።

የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ቅርሶቹ የኢትዮጵያ ሃብቶች ከመሆናቸው በተጨማሪ ለጥናትና ምርምር በግብዓትነት የሚያገለግሉ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
በመላው ዓለም በግለሰቦች እጅ እና በተቋማት ውስጥ የሚገኙና የኢትዮጵያ ታሪክ አስረጂ የሆኑ ጥንታዊ ቅርሶች ወደ ሃገር እንዲመለሱ የማድረጉ ጥረትም ይቀጥላል ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025