🔇Unmute
ጋምቤላ ፤ሕዳር 12/2018(ኢዜአ)፡-በጋምቤላ ክልል ባለፉት አራት ወራት ከ2 ሺህ 798 ኪሎ ግራም በላይ የተጣራ ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ገቢ መደረጉን የክልሉ ማዕድን ሀብት ልማት መስሪያ ቤት አስታወቀ።
በክልሉ ባለፉት አራት ወራት ለብሔራዊ ባንክ የገባው የወርቅ ምርት መጠን ከእቅዱ በ673 ኪሎ ግራም ብልጫ ያለው መሆኑን የማዕድን ልማት መስሪያ ቤቱ ገልጿል።

የጋምቤላ ክልል ማዕድን ሀብት ልማት መስሪያ ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ኡጁሉ ጊሎ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ እንደ ሀገር ለብዝሃ ኢኮኖሚ ተብለው ተለይተው በልዩ ትኩረት እየተሰራባቸው ከሚገኙት ዘርፎች መካከል አንዱ የወርቅ ማዕድን ነው።
ይህን ታሳቢ በማድረግም በክልሉ ለወርቅ ማዕድን ልማቱ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝና በዘርፉም ስኬት እየተመዘገበ መሆኑን ገልጸዋል።

በክልሉ ባለፉት አራት ወራት በዘርፉ በተከናወኑት ስራዎች የህዳር ወር የመጀመሪያ ሳምንትን ጨምሮ ከ2 ሺህ 798 ኪሎ ግራም በላይ የተጣራ ወርቅ ለብሄራዊ ባንክ ገቢ ማድርግ ተችሏል ብለዋል።
ባለፈው አራት ወራት ለብሔራዊ ባንክ ገቢ የተደረገው የወርቅ መጠን ከእቅዱ በ673 ኪሎ ግራም ብልጫ ያለው ሲሆን ከቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ደግሞ ከ1 ሺህ 420 ኪሎግራም በላይ ብልጫ ያለው መሆኑንም ተናግረዋል።
ባለፉት አራት ወራት ለብሄራዊ ባንክ የገባው ወርቅ በክልሉ በሚገኙ የዲማ፣ የአቦቦ፣ የጋምቤላና የመንገሺ ወረዳዎች በባህላዊ፣ ልዩ አነስተኛና በዘመናዊ ኩባንያዎች የተመረተ መሆኑን ገልጸዋል።

በክልሉ በተያዘው በጀት ዓመት አራት ወራት ውስጥ ከእቅድ በላይና ከቀዳሚ ዓመት የተሻለ የወርቅ ምርት ወደ ብሔራዊ ባንክ ሊገባ የቻለው በሀገር አቀፍ ደረጃ በተደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያና በተጠናከረ የክትትልና ድጋፍ ስራ መሆኑን ተናግረዋል።
በቀጣይም የተጀመሩትን ስራዎች ይበልጥ በማጠናከር በበጀት ዓመቱ ለብሔራዊ ባንክ ከ6 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ የተጣራ ወርቅ ለማስገባት የተያዘውን እቅድ ለማሳካት በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025