🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 12/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን በብሔራዊ ፓርኮችና የዱር እንስሳት መጠለያዎች እያከናወናቸው ያሉ አሠራሮች ሕገ ወጥ ድርጊቶች እንዲቀንሱ ማስቻላቸውን ገለጸ።
ባለሥልጣኑ በጀት መድቦ በቀጥታ በሥሩ የሚያስተዳድራቸው 11 ብሔራዊ ፓርኮች እና ሁለት የዱር እንስሳት መጠለያዎች መሆናቸውን አስታውቋል።

በክልሎች ሥር ለሚተዳደሩ ብሔራዊ ፓርኮችም የስልጠና፣ የቁሳቁስና መሰል ድጋፍ እንደሚያደርግ የባለሥልጣኑ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ተወካይ ሥራ አስፈጻሚ ታምሩ መክት ለኢዜአ ተናግረዋል።
የብሔራዊ ፓርክና የዱር እንስሳት መጠለያ ጠባቂዎችን በማሰልጠን፣ ለጥበቃ የሚሆኑ ትጥቆችን በማቅረብ፣ በቂ የሰው ኃይል በማሟላት፣ ካሉበት ሆነው መረጃዎችን የሚለዋወጡበት በቴክኖሎጂ የታገዘ አሠራርን እንዲከተሉ ማድረግ መቻሉን አንስተዋል።
በየአካባቢዎቹ የሚገኙ ነዋሪዎች የኔ ነው ብለው በንቃት እንዲጠብቁ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ መከናወኑንም ጠቁመዋል።

ወጣቶች ተደራጅተው እንዲጠብቁ የማድረግ ሥራ መከናወኑን ጠቁመው፤ ባለሥልጣኑ እየሰራቸው ያሉ አሠራሮች ከሕብረተሰቡ ትብብር ጋር ተቀናጅተው ሕገ ወጥ ድርጊቶች እንዲቀንሱ ማስቻላቸውን ተናግረዋል።
ዓለም አቀፍ ወንጀል የሆነውን ሕገ ወጥ የዱር እንስሳት ውጤቶች ዝውውር ከመቆጣጠር አኳያም፤ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በአነፍናፊ ውሻዎች ጭምር የቁጥጥር ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።
በአነፍናፊ ውሻዎች ታግዞ እየተሠራ ያለው የቁጥጥር ሥራ ውጤታማ መሆኑን አንስተው፤ በዚህም በሕገ ወጥ መንገድ የሚደረግ የእንስሳት ውጤቶች ዝውውር ቀንሷል ነው ያሉት።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025