የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተቋቋሙ የግብይት ማዕከላት የተረጋጋ የገበያ ስርዓት ፈጥረዋል

Jun 30, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሆሳዕና ፤ሰኔ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተቋቋሙ የግብይት ማዕከላት አምራቹንና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘት የተረጋጋ የገበያ ስርዓት እየፈጠሩ መሆኑን አምራቾችና ሸማቾች ገለፁ።

በክልሉ ዱራሜና ወራቤ ከተሞች ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ ሸማቾችና አምራቾች በክልሉ የተቋቁሙ የግብይት ማዕከላት አምራቹንና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘት የተረጋጋ የግብይት ስርዓት እየፈጠሩ ነው ብለዋል፡፡

አስተያየታቸውን ከሰጡ ሸማቾች መካከል የዱራሜ ከተማ ነዋሪው ወንድሙ ዋጠሮ በከተማው የተቋቋሙ የግብይት ማዕከላት ሳምንቱን ሙሉ የግብርናና የፋብሪካ ውጤቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረቡ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ይህም የተረጋጋ ግብይትን በመፍጠር የነጋዴውንም ሆነ የሸማቹን ተጠቃሚነት እያረጋገጡ መሆኑም አክለዋል።


በከተማው በእንስሳት እርባታ ዘርፍ የተሰማሩት ካሰች አዎ በበኩላቸው የከተማው የግብይት ማዕከላት የእንስሳት ተዋፅኦዎችን በተመጣጣኝ ዋጋና በቅርበት ለሸማቹ እንዲያቀርቡ ማስቻላቸውን ገልጸዋል።

ይህም ምርታቸው ሳይበለሽ በጊዜና የማጓጓዟ ወጪያቸውን በቀነሰ መንገድ ሳምንቱን ሙሉ ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።


ከስደት መልስ በጥምር ግብርና ተደራጅታ ስራ መጀመሯን የገለጸችው መኪያ ጀማል በበኩሏ በከተማው የተገነባው ከሰንበት እስከ ሰንበት የግብይት ማዕከል የግብርና ምርታቸውን በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጻለች።

ከዚህ ቀደም ምርቶቻቸውን ወደ ተለያዩ አካባቢዎች ቦታዎች በማጓጓዝ ለገበያ ለማቅረብ የሚፈጅን ግዜና ተጨማሪ የትራንስፖርት ወጪ መቀነስ እንደቻለች አስታውሳለች፡፡

የግብይት ማዕከሉ አምራቹንና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘት በህገወጥ ነጋዴዎችና ደላሎች አማካኝነት በምርት ላይ የሚደረገውን ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ማስቀረቱን ገልፃለች።


የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ባዬሽ ተስፋዬ (ዶ/ር) በበኩላቸው በክልሉ የህብረተሰቡን የኑሮ ደረጃ ያማከለ አገልግሎት የሚሰጡ ግብይት ማዕከላትን የማስፋት ስራ እየከተናወነ ነው ብለዋል፡፡

በክልሉ ከሚገኙ አጠቃላይ የግብይት ማዕከላት ውስጥ 102 የሚሆኑትን ሳምንቱን ሙሉ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል ማዕከላቱን የማዘመን ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

በግብይት ማዕከላቱ ሸማቹንና አምራቹን በማገናኘት በቅናሽ ዋጋ የግብርና፣ የፋብሪካና የኢንዱስትሪ ምርቶች እየቀረቡ ነው ብለዋል፡፡

በዚህም የማህበረሰቡ ተጠቃሚነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ጠቅሰው የኑሮ ውድነቱን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ የግብይት ማዕከላትን የማጠናከር ስራ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረግ ጥረት ይቀጥላል

አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...

Sep 11, 2026

በመደመር መንግሥት ዕይታ አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ራዕይ ተጨባጭ ውጤት አምጥቷል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...

Aug 31, 2026

በአፋር ክልል የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ይጠናከራሉ

ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...

Aug 17, 2026

በሸገር ከተማ አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ ተደርጓል

ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...

Jul 27, 2026