የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

በህዳሴው ግድብ ያሰፈርነውን አሻራ በሀገራዊ ምክክሩ በመድገም ጠንካራ ሀገር ለመገንባት የበኩላችንን ሚና እንወጣለን

Aug 10, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ ፤ነሐሴ 3/2018(ኢዜአ) ፦በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ያሳዩትን የታሪክ አሻራ በሀገራዊ የምክክር ሂደቱ በመድገም ጠንካራ ሀገር በመገንባት ለትውልድ ለማስተላለፍ የበኩላችንን ሚና እንወጣለን ሲሉ ተመካካሪ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ገለጹ፡፡

በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር በመሳተፍ ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በመጎብኘት የተሰማቸውን ደስታና ኩራት መግለጻቸውን ፐልስ ኦፍ አፍሪካ ከስፍራው ዘግቧል፡፡



ከሰሜን አሜሪካ ቨርጂኒያ የመጡት ተመካካሪ አድጎልኝ መኮንን በሰጡት አስተያየት እንደገለጹት፤ ቀደም ሲል ኢትዮጵያ ውስጥ የመንግሥት ሠራተኛ በነበሩበት ወቅት የ400 ብር ቦንድ ገዝተው አስተዋጽኦ ያደረጉበት ግድብ ተጠናቆ በማየታቸው ጥልቅ የደስታ ስሜት ተሰምቷቸዋል።


"ዓባይ ግንድ ይዞ ይዞራል" መባሉ ቀርቶ ዛሬ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ትልቅ የብርሃን ምንጭ መሆን መቻሉ ታላቅ ኩራት ነው ብለዋል።


አሁን ደግሞ ከመላ ኢትዮጵያና ከውጭ ሀገር የተውጣጡ አራት ሺህ ዜጎች በመካከር ላይ መሆናቸውን አውስተው፤ በምክክር ጉባኤው ላይ ስለሀገራቸው ጉዳይ በነጻነት የሚመካከሩበትን ትልቅ ታሪካዊ ዕድል ለመጀመሪያ ጊዜ አግኝተናል ብለዋል።


ዜጎች በመመካከር ጠንካራ ሀገር ለትውልድ ለማስተላለፍ የሚደረገው የሰለጠነ የምክክር ሂደት የሚያስደስት ሆኖ እንዳገኙትም ጠቅሰዋል፡፡


ከሰዊድን የመጡት ተመካካሪ መቅደስ ወርቁ በበኩላቸው፤ በግድቡ ግንባታ ወቅት በውጭ ሀገር ሲያስተባብሩ መቆየታቸውን ገልጸው፤ አሁን ግድቡ ተጠናቆ በአካል ማየት በመቻላቸው ደስታና ኩራት እንደተሰማቸው ተናግረዋል።


በግድቡ የተሰራው ድንቅ ተግባር የኢትዮጵያውያንን ገድል እና ዳግማዊ ዓድዋ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡


አሁን በመካሄድ ላይ የሚገኘው የሀገራዊ ምክክር ሂደት ደግሞ ስር የሰደዱ ችግሮችን በዘላቂነት በመፍታት የኢትዮጵያን ከፍታ እንደሚያረጋግጥም እምነታቸውን ገልጸዋል።


ከእንግሊዝ ሀገር የመጡት ተመካካሪ ኡስታዝ ሙክታር ጀማል፣ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ጉብኝት ወቅት የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ ገልጸዋል።


የታሪካዊ ተቀናቃኞችን እኩይ ሴራ በድል አልፎ በኢትዮጵያውያን ጥረት ብቻ የተገነባውን ይህን ታሪካዊ ግድብ በዕድሜያቸው ማየት በመቻላቸው ታላቅ ኩራት እንደተሰማቸው በስሜት ገልጸዋል።


ከካናዳ ቶሮንቶ የመጡት ተመካካሪ ጌትነት ሃይሉ በበኩላቸው፤ በውጭ ሀገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የወር ደመወዛቸውን ሳይቀር በማዋጣት ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።


በግድቡ ግንባታ ወቅት ዓለም አቀፍ ተቋማት ብድር በመከልከል ጫና ቢፈጥሩም፣ ኢትዮጵያውያን ግን በጋራ በመተባበር ግድቡን በራሳቸው አቅም መገንባታቸው ታሪካዊ ድል መሆኑን ተናግረዋል።


በአሁኑ ወቅት ለትውልድ ጠንካራ ሀገር ለማስተላለፍ የሚያስችላቸውን የምክክር ሂደት መሳተፍ በመቻላቸውም ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸዋል።


የምክክር ሂደቱ ውጤት አብሮነታችንን በማጽናት በተጠናከረ መልኩ በጋራ ለልማት መነሳሳት እንደሚቻል እምነታቸውን ገልጸዋል።



የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍፁም አረጋ፤ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ቦንድ በመግዛት፣ በስጦታ እና በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ስለግድቡ በመከራከር ያደረጉትን አስተዋጽኦ አድንቀዋል።


በአሁኑ ወቅት ግድቡ የኤሌትሪክ ሃይል ያልደረሳቸው ቀበሌዎች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ እንዲሆኑ፣ ለከባድ ኢንዱስትሪዎች እና ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠሩን ገልጸዋል።


ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በንጋት ሐይቅ ዙሪያ የተፈጠሩትን ደሴቶች እና የቱሪዝም ፀጋዎች በመመልከት በቱሪዝም ኢንቨስትመንት እንዲሳተፉም ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረግ ጥረት ይቀጥላል

አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...

Sep 11, 2026

በመደመር መንግሥት ዕይታ አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ራዕይ ተጨባጭ ውጤት አምጥቷል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...

Aug 31, 2026

በአፋር ክልል የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ይጠናከራሉ

ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...

Aug 17, 2026

በሸገር ከተማ አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ ተደርጓል

ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...

Jul 27, 2026